ሚያዝያ 24/25 በድምቀት ይመረቃል

- Advertisement -
Sidebar AD

ማረፊያና ማለፊያው ደብር

በጉራጌ ምድር ጠርዙን ይዞ የቆመው የምሁር ኢየሱስ ገዳም፣ ከምድራዊው ዓለም ይልቅ ወደ ሰማያዊው መንግሥት የቀረበ ይመስላል።
ወደ ቅጽረ ግቢው ሲዘልቁ ነፍስን የሚያረሰርሱ፣ ሥጋን የሚያሳርፉ ድንቅ ትዕይንቶች በፊቱ ይዘረጋሉ።

ጥንታውያንና ግርማ ሞገስ የተላበሱት የገዳሙ ዛፎች፣ እንደ ዘበኛ ቆመው ጥላን ይግታሉ። ነፋሱ በቅጠሎቻቸው መካከል ሲያልፍ የሚፈጥረው “ሹክሹክታ” ለፀሎት የሚጋብዝ ረቂቅ ድምፅ አለው።

በቅርንጫፎቹ ላይ የሚረግጡት አእዋፍ፣ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርቡ ይመስል በልዩ ዜማቸው የገዳሙን ሰላም ያደምቁታል። ዝማሬያቸው ከገዳሙ መንፈሳዊነት ጋር ተዋህዶ የነፍስ ምግብ ይሆናል።

የገዳሙ አቀማመጥና የሕንፃው ጥበብ የአባቶቻችንን የታሪክ አሻራ በጉልህ ያሳያል። ከሩቅ ሲታይ የማማው ግርማ፣ በውስጥ ሲታይ ደግሞ የቅድስናው ድባብ የሰው ልጅን ልብ በአድናቆት ይሞላል።

በዚያ የተቀደሰ ስፍራ የካህናቱ ዝማሬ ሲሰማ፣ ምድራዊው ድምፅ ጠፍቶ ሰማያዊ ዜማ የተጀመረ ይመስላል። በጥበብና በትሕትና የተሞላው አስተምሯቸው ደግሞ የጠፋውን የሚመልስ፣ የደከመውን የሚያጸና የመንፈስ ብርሃን ነው።

ምሁር ኢየሱስ ገዳም ተፈጥሮ ከፈጣሪዋ ጋር የተገናኘችበት፣ ሰው ከራሱ ጋር የታረቀበት፣ በቅድስናና በውበት የተከበበ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የከበረ ዕንቁ ነው።
ለዚህ ምረቃ በዓል መብቃት እንደ ፀሃይ ብርሃን ነው። አንድም ጠዋት ሁለትም ቀትር ሆኖ ፍንትው ብሎ መታየት።

ምንጭ 👉እንዳልካቸው ደሳለኝ
ያለን ቦታ ጥቂት ነው ፈጥነው ይመዝገቡ
አዘጋጅ ምሁር ኢየሱስ ገዳም
ቅዱስ ዳዊት የበገና ቤተሰብ ጋር ይጓዙ
0911358560/0911083713
0921327074 /0913383033


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: