ሶማሊላንድ በሁቲ ላይ ከእስራኤል ጋር ለመተባበር ፍላጎት አሳየች
ራስ ገዟ ሶማሊላንድ በየመን የሚገኙትን ሁቲን እንደ “የጋራ ጠላት” በመቁጠር፣ ቀጠናዊ ደህንነትን ለመጠበቅ ከእስራኤል ጋር የጸጥታ ጥምረት ለመመስረት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች።አንድ ከፍተኛ የሶማሊላንድ ባለስልጣን ለእስራኤል ቻናል 12 እንደተናገሩት፣ ሁቲዎች በባህር ላይ የሚያደርሱት ጥቃት የቀጠናውን ጸጥታ የሚያናጋ በመሆኑ ከእስራኤል ጋር ወታደራዊ ትብብር ማድረግ ለሁለቱም ወገኖች ጠቃሚ ነው።
ሶማሊላንድ ከዓለም አቀፍ ንግድ 12 በመቶው በሚያልፍበት የ”ባብ አል-መንደብ” የባህር ወሽመጥ አቅራቢያ የምትገኝ መሆኗ ለጥምረቱ ትልቅ ፋይዳ አለው። አገሪቱ በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (UAE) ከሚመራው ጥምረት ጋር እየሰራች ሲሆን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በበርበራ ወደብ ላይ ወታደራዊ መገኘት እንዳላት ይታወቃል።
ይህ እርምጃ ሶማሊላንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዲፕሎማሲያዊ እውቅና ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት እና በቀጠናው ላይ ያላትን ተፅዕኖ ለማሳደግ የምትጠቀምበት አዲሱ ስልትዋ መሆኑ ነው።
@seledadotio

No comments yet.