ሕወሃት አዲስ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ነው – አቶ ጌታቸው ረዳ
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ሕወሃት አዲስ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ነው በማለት ከባድ ክስ ሰነዘሩ።
አቶ ጌታቸው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መረጃ፣ የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አዲስ ዓለም ባሌማ ለዲያስፖራው በሰጡት ገለጻ ሕወሃት ከሌሎች አማጺያንና ከኤርትራ መንግሥት ጋር በመቀናጀት ለጦርነት መዘጋጀቱን መናገራቸውን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ቡድኑ የሱዳን ወደቦችን ለመጠቀም ከሱዳን መንግሥት ፈቃድ ማግኘቱን መግለጣቸውን በማጋለጥ፣ ይህ ድርጊት “ግልጽ የፖለቲካ ትንኮሳ” ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
አቶ ጌታቸው አክለውም፣ ሌላ ዙር ጦርነት በትግራይ ላይ የሚያስከትለው ውጤት የከፋና የቀሩትን ጥቂት ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ መሠረቶች ጨርሶ የሚያወድም መሆኑን አስጠንቅቀዋል። የሕወሃት አመራሮች ከጦርነት ቅስቀሳ ወጥተው ትኩረታቸውን ክልሉን መልሶ በማቋቋም ላይ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.