ከሁለት አባት ከአንድ እናት የተወለዱ መንትዮች

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ላቪኒያ እና ሚሼል ኦስቦርን የተባሉ መንታ ልጆች በተደረገላቸው የዲኤንኤ ምርመራ የተለያዩ አባቶች እንዳሏቸው ተረጋገጠ። ይህ በሕክምናው ዓለም “Heteropaternal Superfecundation” ተብሎ የሚጠራው ብርቅዬ ክስተት፣ በዩናይትድ ኪንግደም በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰነድ የተመዘገበ የመጀመሪያው ጉዳይ ሆኗል።

​በአሁኑ ወቅት ዕድሜያቸው 49 ዓመት የሆኑት እነዚህ መንታ እህቶች፣ ሚስጥሩ ሊታወቅ የቻለው ሚሼል ኦስቦርን እ.ኤ.አ. በ2022 ባደረገችው የDNA ምርመራ ነው። ምርመራው ሁለቱም እህቶች በአንድ ማህፀን አብረው ቢያድጉና በደቂቃዎች ልዩነት ቢወለዱም፣ ባዮሎጂካዊ አባቶቻቸው ግን የተለያዩ መሆናቸውን አረጋግጧል።

​ክስተቱ ሊከሰት የቻለው እናታቸው በአንድ የወር አበባ ዑደት ውስጥ ከአንድ በላይ እንቁላል አፍርታ፣ በተለያዩ የግብረ-ሥጋ ግንኙነቶች አማካኝነት በተለያዩ ወንዶች ዘር እንዲዳበሩ በመደረጉ እንደሆነ ተገልጿል። በዓለም አቀፍ ደረጃ እስካሁን የተመዘገቡት እንዲህ ዓይነት ክስተቶች ከ20 የማይበልጡ በመሆናቸው ጉዳዩን እጅግ አስገራሚ አድርጎታል ይላል የቢቢሲ ዘገባ።

​ላቪኒያ እና ሚሼል አስቸጋሪ የልጅነት ጊዜን አብረው ያሳለፉ ሲሆን፣ ውጤቱ መጀመሪያ ላይ አስደንጋጭ ቢሆንባቸውም አሁንም ያላቸው “የመንትያነት” ትስስር የማይበጠስ መሆኑን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ሁለቱም እህቶች የየራሳቸውን እውነተኛ አባቶች ማግኘት የቻሉ ሲሆን፣ ላቪኒያ ከአባቷ ከአርተር ጋር የጠበቀ ግንኙነት መመሥረት ችላለች።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: