በኢራን ግጭት ሳቢያ የኮንዶም ዋጋ እስከ 30 በመቶ ሊጨምር ነው
በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው የኢራን ግጭት በዓለም አቀፍ የጤና ምርቶች ላይ ጫና ማሳደሩን ቀጥሏል። የዓለማችን ግዙፉ የኮንዶም አምራች ካሬክስ እንደገለጸው በጦርነቱ ሳቢያ በሚፈጠሩ የግብዓት እጥረት እና የትራንስፖርት መስተጓጎሎች ምክንያት የኮንዶም ዋጋ ከ20 እስከ 30 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ሊያሳይ እንደሚችል አስታውቋል።
ለዚህ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በምክንያትነት የተጠቀሱት ዋና ዋና ጉዳዮች ለምርቱ ማቀነባበሪያ እና ለቅባት የሚያገለግሉ እንደ ሲሊኮን ዘይት፣ አሞኒያ እና ናይትሬል ያሉ የፔትሮኬሚካል ውጤቶች አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ መመታቱ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በስትሬት ኦፍ ሆርሙዝ አካባቢ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት የመርከብ ጭነት ዋጋ የጨመረ ሲሆን ምርቶችን መዳረሻ ለማድረስ የሚፈጀው ጊዜም በእጥፍ አድጓል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የምርት እጥረት ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት የገዢዎች ፍላጎት በ30 በመቶ መጨመሩም በገበያው ላይ ተጨማሪ ጫና ፈጥሯል።
ካሬክስ ለዓለም አቀፍ የጤና ድርጅቶች እና ለታወቁ ብራንዶች ዋነኛ አቅራቢ በመሆኑ ይህ የዋጋ ጭማሪ በተለይ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የመከላከያ ምርቶችን በቅናሽ ዋጋ ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት ያደናቅፋል ተብሎ ተፈርቷል።
ይህም ካልተፈለገ እርግዝና እና ከአባላዘር በሽታዎች መከላከል ጋር ተያይዞ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋትን ሊደቅን እንደሚችል ባለሙያዎች በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው።
@seledadotio

No comments yet.