#Ethiopia | ደቡብ አፍሪካ በአህጉሪቱ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) መሪ ለመሆን የነደፈችው ብሄራዊ ፖሊሲ፣ ሰነዱ በራሱ በ AI የተፈጠሩ “ሀሰተኛ መረጃዎች” ተገኝተውበት ውድቅ ተደረገ።
የሀገሪቱ የኮሙኒኬሽን እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሶሊ ማላትሲ እንደተናገሩት፣ ረቂቅ ፖሊሲው ለፓርላማ ቀርቦ ሊጸድቅ ጥቂት ሲቀረው በውስጡ የተካተቱ የምንጭ ማስረጃዎች ፈጽሞ የሌሉ እና በ AI አማካኝነት በዘፈቀደ የተፈጠሩ መሆናቸው ታውቋል።
ይህ አይነቱ ስህተት ተራ ቴክኒካዊ ግድፈት ሳይሆን የፖሊሲውን አጠቃላይ ታማኝነት እና ተአማኒነት አደጋ ላይ የጣለ ተግባር መሆኑን ሚኒስትሩ በቁጭት ገልጸዋል።
ይህ አጋጣሚ የ AI ቴክኖሎጂን ስንጠቀም የሰዎች የቅርብ ክትትል እና ማረጋገጫ ምን ያህል ወሳኝ መሆኑን በተግባር ያሳየ ትምህርት ሆኖ ተወስዷል።
ቀድሞ ተዘጋጅቶ የነበረው ፖሊሲ ብሄራዊ የ AI ኮሚሽንን፣ የሥነ-ምግባር ቦርድን እና የቁጥጥር ተቋምን ለማቋቋም እንዲሁም ለግል ዘርፉ የግብር ማበረታቻዎችን ለመስጠት ያለመ ነበር።
ሆኖም የምንጭ ማስረጃዎቹ ያለምንም የሰው ልጅ ክትትል በ AI ቻትቦቶች መመረታቸው ለፖሊሲው መክሸፍ ምክንያት ሆኗል።
በዓለም ዙሪያ ያሉ የሕግ ሰነዶች ላይ ተመሳሳይ ችግሮች እየታዩ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ሚኒስትር ማላትሲ ረቂቁ በድጋሚ ተዘጋጅቶ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ ባይገልጹም፣ ክስተቱ በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷነው
ዘገባው የcapital ነው
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.