#Ethiopia | በውቧ ባህር ዳር ከተማ በከፍተኛ ወጪ የተገነባው ግዙፉ የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ዛሬ ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ስነ ስርዓት ተመርቋል።
በደቡባዊ የጣና ሀይቅ ዳርቻ ላይ ያረፈው ይህ ሪዞርት በጎርጎራ በኩል የተጀመረውን የቱሪዝም ልማት ብርሃን ወደ ሌላኛው የሀይቁ ዳርቻ ያሸጋገረ ግዙፍ ኢንቨስትመንት ነው።
ፕሮጀክቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በገበታ ለሀገር እቅድ አማካኝነት ሁለት የጣና ሀይቅ ዳርቻዎችን በቱሪዝም ለማስተሳሰር የነደፉትን ታላቅ ራዕይ ዳር ያደረሰ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታሪካዊቷን የጎርጎራ ከተማ ገፅታ ከመቀየር ባለፈ በዐፄ ፋሲለደስ መናገሻ ጎንደር የሚገኙ የቤተ መንግስት ቅርሶችን በከፍተኛ ጥራት በማደስ ለዘላቂ ቱሪዝም ዝግጁ እንዲሆኑ አድርገዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ለጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ለግብርና ልማት የሚውለው የመገጭ ግድብ ግንባታ ለውሃ ቱሪዝም አዲስ እድል ይዞ እየመጣ ይገኛል።
ይህንን መንግስታዊ ራዕይ በግል ኢንቨስትመንት በማገዝ የቤአኢካ እና የእህት ኩባንያዎቹ መስራች አቶ ካሳሁን ምስጋናው የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርትን በ 4.5 ቢሊዮን ብር ወጪ በሁለት አመት ከስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ገንብተው አጠናቀዋል።
ግለሰቡ በጎርጎራ ኢኮ ቱሪዝም ግንባታ እና በጎንደር ቅርሶች ጥገና ላይ የነበራቸውን ውጤታማ ተሳትፎ አሁን ደግሞ በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ውስጥ በሮዳ ሆስፒታሊቲ ግሩፕ በኩል በስፋት ለመቀጠል ተዘጋጅተዋል።
አቶ ካሳሁን ለእነዚህ ስራዎች ስኬት የፌዴራል እና የክልል መንግስታት እንዲሁም የከተማ አስተዳደሮች ላደረጉላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ወደፊትም የፈለገ ግዮን እና የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርቶች በሮዳ ሆስፒታሊቲ ግሩፕ ስር በመሆን ልባችን ኢትዮጵያ ደረጃችን አለም አቀፍ በሚል መሪ ቃል ጥራት ያለው አገልግሎት ለጎብኚዎች እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
#bahirdar #tanalake #tourismethiopia #beaikainvestment #rodahospitality #development #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen









No comments yet.