ኢራን ‘ለአሜሪካ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

- Advertisement -
Sidebar AD

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ከ”ሰኞ ጠዋት” ጀምሮ መርከቦችን ማስወጣት እንደሚጀምር መግለጻቸውን አስመልክቶ ኢራን ምላሽ ሰጥታለች።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወሽመጡ ዙሪያ “ለአሜሪካ ዛቻዎች ምላሽ ለመስጠት” ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል።
ሜህር የዜና ወኪል ባጋራው መግለጫ ቃል አቀባዩ ኢስማኤል ባጋይ ኢራን የባህር ወሽመጡ “ጠባቂ እና ተከላካይ” ሆና ትቀጥላለች ብለዋል። “መርከቦች እና የመርከብ ኩባንያዎች ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ከኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ባለስልጣናት ጋር መተባበርን እንደሚጠይቅ በሚገባ ያውቃሉ” ሲሉ አክለዋል።
የሕግ የበላይነትን የሚከተሉ አገሮች የአሜሪካን “ሕገወጥ እርምጃዎች” የሚከተሉበት ምንም ምክንያት እንደሌለም ተናግረዋል።

ቀደም ሲል የኢራን ማዕከላዊ ዕዝ ኃላፊ “በተለይም ጠበኛው የአሜሪካ ጦርን” ጨምሮ ወደ ባህር ወሽመጡ ለመቅረብ ወይም ለመግባት የሚሞክርን “ማንኛውም የውጭ የጦር ኃይል” እንደሚያጠቃ ተናግረዋል።

BBC




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: