በሀረር አንዲት እናት አምስት ልጆችን ተገላገሉ
በሐረሪ ክልል በሐረር ከተማ አንዲት የ35 ዓመት እናት አራት ወንድ እና አንድ ሴት በድምሩ አምስት ሕፃናትን (Quintuplets) በሰላም መገላገሏ ተገለጸ።
ወይዘሮ በድሪያ አደም የተባሉት እነዚህ እናት፣ ዛሬ ምሽት 3፡30 አካባቢ በሐረር ሕይወት ፋና ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች በሰጡት ድጋፍ ሕፃናቱን በሰላም ሊያገኙ ችለዋል።
እናትየው በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቂሌ ቀበሌ “ገንደ አህመድ” ተብሎ በሚጠራው መንደር ነዋሪ ሲሆኑ፤ ትዳር መሥርተው በቆዩባቸው 12 ዓመታት ውስጥ ልጅ የመውለድ ፍላጎታቸው ሳይሳካ መቆየቱ ተገልጿል።
ይሁንና አሁን ላይ በአንድ ጊዜ የአምስት ሕፃናት እናት ለመሆን በቅተዋል።
የሕክምና ባለሙያዎቹ እንደገለጹት ከሆነ፣ በአሁኑ ወቅት አምስቱም ሕፃናት (4 ወንድ እና 1 ሴት) በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።
ሕፃናቱ አስፈላጊው ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት በማሞቂያ ክፍል (Incubator) ውስጥ እንደሚገኙም ታውቋል።
ይህ ልዩ ክስተት በሆስፒታሉ ባለሙያዎችና በቤተሰቦቻቸው ዘንድ ትልቅ ደስታን የፈጠረ ሲሆን፣ እናትየውም በሰላም መገላገላቸው ተረጋግጧል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.