ከጀርመን እስከ ኢትዮጵያ የዘለቀው የፅናት እና የፍቅር ጉዞ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከጀርመን እስከ ኢትዮጵያ የተዘረጋው የሕይወት ጉዞ በመከራ ውስጥ ማለፍን፣ መውደቅን እና ዳግም መነሳትን ያስመሰከረ የፅናት መንገድ ሆኖ ተመዝግቧል።

አርቲስት አብርሃም ፀጋዬ ከመምህርነት እስከ ሥዕልና ቅርፃቅርፅ እንዲሁም እጅግ በሚወደውና በተፈተነበት የመና ፈርኒቸር ሥራ ውስጥ ያለፈባቸው ውጣ ውረዶች ለዛሬው የድል ቀን መነሻ ሆነውታል።

ተስፋ አስቆራጭ የሆኑ የሥራ መሰናክሎችን እና የሕይወት አጣብቂኞችን በትግልና በእምነት ተሻግሮ ለምስጋና መብቃቱን ገልጿል።

በተለይም ሕይወትን እስከማጥፋት የሚያደርሱ ከባድ ፈተናዎችን በልጁ ሳቅ እና በእናቱ ጸሎት ታግዞ ማለፍ መቻሉን የገለጸው አብርሃም፣ ለዚህ ሁሉ ስኬት የሕይወት አጋሩ የሆነችው ሕሊና ያዕቆብ ላሳየችው እውነተኛ ፍቅርና ታማኝነት ምስጋናውን አቅርቧል።

በፈተና ወቅት አብሮነታቸውን ላልነፈጉት ወዳጅ ዘመዶቹ እና በማኅበራዊ ሚዲያ ለሚያበረታቱት ሁሉ ምስጋናውን በማቅረብ ምንም ዓይነት ከባድ መሰናክል ቢገጥም በእግዚአብሔር ተስፋ በማድረግ መሻገር እንደሚቻል ለሌሎችም ብርታትን የሚሰጥ መሆኑን አርቲስት አብርሃም ፀጋዬ መልዕክቱን አስተላልፏል።

አብርሃም ፀጋዬ እና ሕሊና ያዕቆብ
እንኳን ደስ አላችሁ
መልካም ጋብቻ🙏

#AbrahamTsegaye #LifeJourney #Inspiration #Resilience #Faith #EthiopianArtist #MenaFurniture #SuccessStory
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2