በአማራ ክልል ከ99 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ይወስዳሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

በአማራ ክልል ከ99 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ጥላሁን ወርቅነህ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ፈተና 99 ሺህ 900 ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ዘርፈ ብዙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ተማሪዎች የስነ ልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በስነ ልቦና ምሁራን የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ፤ ከመደበኛው የክፍል ትምህርት በተጨማሪ የማካካሻ ትምህርቶችንና ሞዴል ፈተናዎችን የመስጠት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ፈተናውን መቶ በመቶ በበይነ-መረብ ለመስጠት የታቀደውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ክልሉ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም መሠረት በየደረጃው ያሉ ኮምፒውተሮችን የመጠገን፣ አዳዲስ ግዢዎችን የመፈጸምና የኢንተርኔት መሠረተ-ልማት የማሟላት ስራዎች በስፋት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በፈተና ወቅት የኤሌክትሪክ ኃይልና የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ እንዳያጋጥም ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ሌሎች አጋር አካላትን ያካተተ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ተግባር መግባቱንም አመላክተዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመማሪያ መጽሐፍ አቅርቦት ለአንድ ተማሪ አንድ መጽሐፍ በሚል ደረጃ ተደራሽ መደረጉ ለተማሪዎቹ ዝግጅት ትልቅ አቅም ፈጥሯል ሲሉ አስረድተዋል።

#ጋዜጣፕላስ



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2