ሜሪ ጆይ እና ሄዋን ፋውንዴሽን በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች የቤተሰብ ድጋፍ ፕሮግራም ይፋ አደረጉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከሄዋን ፋውንዴሽን ጋር በመቀናጀት በተለያዩ ችግሮች ሳቢያ ከቀያቸው ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኙ መጠለያዎች ውስጥ ለሚገኙ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው የሚውል የቤተሰብ ስፖንሰርሺፕ መርሃ ግብር በይፋ አስጀምረዋል።

ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እና ሄዋን ፋውንዴሽን ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የተጎጂዎችን፣ ተፈናቃይ ህፃናትን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን እና አረጋውያንን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል የድጋፍ ፕሮጀክት መክፈቻ ስነ ስርዓት አካሂደዋል።

በዚሁ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፣ የከተማው የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ጌታቸው፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምርያ ኃላፊ ወይዘሮ በለጥሽ ግርማ፣ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ እንዲሁም የሄዋን ፋውንዴሽን ባለቤት ወይዘሮ ሄዋን ቀለመወርቅ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በወቅቱም ለህፃናትና ለቤተሰቦቻቸው አልባሳት፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች እና የምግብ አይነቶች ተከፋፍለዋል።

የሄዋን ፋውንዴሽን መስራች ወይዘሮ ሄዋን ቀለመወርቅ በማህበራዊ ሃላፊነት ዙሪያ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ማህበራዊ ግዴታን መወጣት የሁሉም ዜጋ ድርሻ መሆኑን ጠቅሰው በደብረ ብርሃን የሚገኙ ህፃናት ብቻቸውን እንደማይሆኑና ርሀብ እንዳይጠናወታቸው የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

#ሜሪጆይ #ሄዋንፋውንዴሽን #ደብረብርሃን #ሰብአዊድጋፍ #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: