#Ethiopia | የአዋሽ ኤፍ ኤም ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አብዱ መሀመድ የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ተገኝተው የለውጡ መንግስት በዘርፉ ላይ ያመጣቸውን አዎንታዊ ለውጦች በዝርዝር አብራርተዋል።
የሚዲያው ዘርፍ ቀደም ባሉት ጊዜያት በፖለቲካዊ ጫናዎች፣ በሙያዊ ብቃት ማነስ፣ በፋይናንስ እጥረት እና በቴክኖሎጂ ኋላቀርነት በእጅጉ ተፈትኖ መቆየቱን ስራ አስኪያጁ አስታውሰዋል።
እነዚህን ስር የሰደዱ እንቅፋቶች ለመቅረፍ መንግስት የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያዎችን በማድረግ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ዶክተር አብዱ ገልጸዋል።
በዘርፉ ላይ ለኢንቨስትመንት ትኩረት መሰጠቱ የሬዲዮ ጣቢያዎች ቁጥር እንዲበራከት ከማድረጉም በላይ ሚዲያዎች የጋራ እሴቶችን በማጎልበት፣ ማህበረሰብን በማስተሳሰር እና በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ተገቢውን ሚና እንዲወጡ ትልቅ አቅም መሆኑን ጠቁመዋል።
#awashfm #media #ethiopianews #discussion #nationalgrowth #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.