ቡሩኖ ፈርናንዴዝ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የእግር ኳስ ፀሀፊዎች ማህበር ብሩኖ ፈርናንዴዝን የአመቱ የፕሪሜር ሊግ ምርጥ ተጫዋች ብሎ መርጧል።

የማንቸስተር ዩናይትድ አንበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ በእንግሊዝ የእግር ኳስ ጸሐፊዎች ማህበር (FWA) የዓመቱ ምርጥ ወንድ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ።

ፖርቹጋላዊው አማካይ በዚህ የውድድር ዘመን ለቀይ ሰይጣኖቹ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው 34 ጨዋታዎች 8 ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ፣ 20 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን (አሲስት) አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ፈርናንዴዝ ቡድኑ በጊዜያዊ አሰልጣኙ ማይክል ካሪክ ስር ላሳየው የተሻሻለ አቋም ቁልፍ ሚና መጫወቱ ተገልጿል።

ምንም እንኳን ማንቸስተር ዩናይትድ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት የውድድር ዘመኑን ያለ ዋንጫ የሚያጠናቅቅ ቢሆንም፣ በፕሪምየር ሊጉ በሶስተኛ ደረጃ ላይ በመገኘት የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማረጋገጥ ተቃርቧል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ እ.ኤ.አ. በ2010 ይህንን ሽልማት ካሸነፈው ዋይን ሩኒ በኋላ የFWA የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ክብርን የተቀዳጀ የመጀመሪያው የዩናይትድ ተጫዋች ሆኗል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1