ብሩክ ጫላ በናይሮቢው የአፍሪካ-ፈረንሳይ የፈጠራ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን እየወከለ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I “ብሩክ ኒውስ” (Brook News) ብሩክ ጫላ በናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው የ #AfricaForward Summit ላይ የኢትዮጵያን የዲጂታል ዜና ዘርፍ በመወከል በመሳተፍ ላይ ይገኛል።

በቲክቶክ እና በፌስቡክ ገጾቹ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮችን ማፍራት የቻለው ብሩክ፣ በተለይም አጫጭር የቪዲዮ መረጃዎችን፣ ሰበር ዜናዎችንና በወቅታዊ የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው መረጃዎች ይታወቃል። ብሩክ ከሚዲያ ስራው በተጓዳኝ በሙያው መሃንዲስና የዩኒቨርሲቲ መምህር ሲሆን፣ በዘንድሮው ጉባኤ ላይ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች በፈጠራ፣ በወጣቶች ተሳትፎና በአፍሪካ-ፈረንሳይ የትብብር ማዕቀፎች ዙሪያ ያላቸውን ሚና በተመለከተ ሰፋ ያሉ ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል።

ይህ በናይሮቢ ኬንያ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ፣ በአፍሪካና በፈረንሳይ መካከል ያለውን የፈጠራና የኢኮኖሚ እድገት ትስስር ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፣ እንደ ብሩክ ያሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ የዲጂታል ድምጾች መገኘት መረጃው ለብዙሃኑ ተደራሽ እንዲሆን ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ አስታውቋል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2