ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጋና፣ከአይቮሪኮስትና ከኮንጎ ብራዛቪል ያስመጣቸውን አራት ተጫዋቾች በይፋ አስፈርሟል

- Advertisement -
Sidebar AD

✌️

✌️”ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ ሲሉኝ አልደሠትም፤ምክንያቱም ኢትዮጵያ ሀገሬ፤ጊዮርጊስም ቤቴ ነው”አሠልጣኝ ሚቾ

👉”እኔ የጊዮርጊስ አሠልጣኝ የሆንኩት በትምህርት ዝግጅቴም፣በልምዴም ይሄንን ኃላፊነት መሸከም ትችላለህ ተብዬ ታምኖብኝ እንጂ ውለታ ተውሎልኝ አይደለም”አሠልጣኝ ፋሲል

#Ethiopia | አንጋፋውና ታላቅ የውጤታማነት ታሪክ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጋና፣ከአይቮሪኮስትና ከኮንጎ ብራዛቪል ያስመጣቸውን አራት ተጫዋቾች ዛሬ በሸራተን ኢንተርናሽናል አዲስ ሆቴል በተካሄደ ስነ-ስርዓት በይፋ አስፈርሟል።

ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀውና በሸራተን አዲስ በተከናወነው የፊርማና የትውውቅ ስነ-ስርዓት አልፍሬድ ሜንሳህ(አጥቂ)፣ኬልቪን ኤዶ ዶሴህ(ተከላካይ)ሁለቱም ከጋና፣ካርተር አሂሮ(ተከላካይ)ከአይቮሪኮስት እና ክረስት ቶሉንጋ ከኮንጎ ብራዛቪል ወደ ክለቡ ያዘዋወራቸውን አራት ተጫዋቾች በማስፈረም ከዚህ በኋላ የክለቡ ንብረት መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በፊፋ የተጣለበት ተጫዋች የማዘዋወር ዕግድ መነሳቱን ተከትሎ ለክለቡ የፈረሙት አራቱም ከባህር ማዶ የመጡት ተጫዋቾች በዛሬው ዕለት ቡድኑን በመቀላቀል ልምምዳቸውን የሠሩ ሲሆን በቀጣይ ጨዋታ የመሠለፍ ዕድል ሊያገኙ እንደሚችሉ ይጠበቃል።

በፊርማ ስነ-ስርዓቱና በትውውቅ ፕሮግራሙ ላይ አስተያየቱን የሠጠው የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ”በጣም ጭንቅ ውስጥ ቆይተን፣ያን ሁሉ መከራ አልፈን አራት ተጫዋቾችን ማስፈረም መቻላችን ትልቅ ዕድል ነው፤በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት የተለመደው ሻምፒዮናነት በመሆኑ ሁለተኛ ደረጃ እንኳን ብዙም ቦታ አይሠጠውም፤አሁን የተሻለ ደረጃ ይዘን ማጠናቀቅ አለብን”ሲል ተጫዋቾች አስመጥተው በማስፈረማቸው መደሠቱን ከመግለፁ ውጪ ይሄ እንዲሆን ያደረጉትን በሙሉ በተለይ ሚድሮክንና ዋና ስራ አስፈፃሚውን አቶ ጀማል አህመድን አመስግኗል።

“እኔ የጊዮርጊስ አሠልጣኝ የሆንኩት በትምህርት ዝግጅቴም፣በልምዴም ይሄንን ኃላፊነት መሸከም ትችላለህ ተብዬ ታምኖብኝ እንጂ ውለታ ተውሎልኝ አይደለም፤ይሄንን ቀግልፅ መናገር እፈልጋለሁ”ብሏል ፋሲል ቀአስተያየቱ መጨረሻ።

የቀድሞ የክለቡ አሠልጣኝ ሚቾ በተደጋጋሚ ከቡድኑ ጋር በመታየታቸውና በዛሬው የፊርማ ስነ-ስርዓትም ከኮቺንግ ስታፉ ጋር መድረክ ላይ በመታየታቸው በቀጣይ ቡድኑን ሊረከቡ ነው እንዴ?የሚል ጥያቄ በብዙዎች አእምሮ ውስጥ ቢፈጠርም አሠልጣኝ ሚቾ ግን “እመኑኝ በፍፁም ይሄ የማይሆን ነው፤የአራት ሀገራት ብ/ቡድንን ለማሠልጠን በሚደረግ ፉክክር በአራቱም ሾርት ሊስት (የመጨረሻ ዕቅድ) ውስጥ ነኝ”በማለት ጥርጣሬውን ወይንም የይሆናል መላምቱን የገፈፈ ቁርጥ ያለ ምላሽ ሠጥተዋል።

“ብዙ ሠዎች ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ ሲሉኝ እንደዚህ አትበሉኝ ነው የምለው ምክንያቱም ኢትዮጵያ ሀገሬ ናት፤ጊዮርጊስም ቤቴ ነው”በማለትም ሰርቢያዊው ሚቾ ጨምረው ተናግረዋል።

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2