አስቸኳይ የህይወት አድን የህክምና እርዳታ ጥሪ
#Ethiopia | በፅናት የካንሰር ህመምን እየተጋፈጠች ለምትገኘውና የሁለት ልጆች እናት ለሆነችው ወይዘሮ የሺእመቤት ንጉሴ አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ ቀርቧል።
ወይዘሮ የሺእመቤት እ.ኤ.አ በ2023 ማርች ወር ላይ የማህፀን ዕጢ እንዳለባት ታውቆ በቀዶ ጥገና ህክምና ክትትል ስታደርግ የቆየች ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ህመሙ በከፍተኛ ሁኔታ አገርሽቶባታል።
በማርች 2026 በናይሮቢ አጋ ካን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በተደረገላት የላቀ የፒኢቲ ሲቲ ምርመራ ካንሰሩ ወደ ሳምባዋ፣ ጉበቷ እና ሆድ ዕቃዋ መሰራጨቱ ተረጋግጧል።
የህክምና ባለሙያዎች ህይወቷን ለመታደግ እጅግ ዘመናዊ እና ተስፋ ሰጭ የሆኑ የመድኃኒት ህክምናዎችን እንድትጀምር የወሰኑ ቢሆንም እነዚህ መድኃኒቶች በየሶስት ሳምንቱ የሚወሰዱና እጅግ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ በመሆናቸው ከቤተሰቧ አቅም በላይ ሆኗል።
በመሆኑም ደግ ኢትዮጵያውያን ለዚች እናት የህይወት ተስፋ እንድትሆኑና በገንዘብም ሆነ መረጃውን በማጋራት ከጎኗ እንድትቆሙ ጥሪ ተላልፏል።
ለመርዳት የምትፈልጉ ወገኖች በሚከተሉት የባንክ ሂሳቦችና የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000131098816 የሺእመቤት ንጉሴ
የአቢሲኒያ ባንክ
97406863 የሺእመቤት ንጉሴ
የጎፈንድሚ ሊንክ
https://gofund.me/6cd261620
#ጤና #እርዳታ #ደግነት #ኢትዮጵያ #ካንሰር #ህክምና #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen









No comments yet.