በትግራይ ክልል የመንግስት ስያሜ እና አርማ አጠቃቀም ላይ አዲስ መመሪያ ተላለፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በትግራይ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በወጣ ይፋዊ ደብዳቤ፣ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የዞን እና የወረዳ አስተዳደሮች ከግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ህገ-መንግስታዊ ስያሜን፣ ብሄራዊ አርማን እና ማህተምን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ።

​የክልሉ ምክር ቤት በሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ወደ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ለመመለስ መወሰኑ ይታወሳል። በዚህም መሰረት ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲሰራበት የነበረው የጊዜያዊ አስተዳደር መዋቅር የክልል መንግስት መተካቱ ተገልጿል።

​ይህንን ተከትሎም ማንኛውም የመንግስት ተቋም በሚያደርጋቸው ኦፊሴላዊ ግንኙነቶች፣ የደብዳቤ ራስጌዎች (Letterheads) እና ማህተሞች ላይ “የጊዜያዊ አስተዳደር” የሚሉ ስያሜዎችን በመተው፣ የቀድሞውን ህገ-መንግስታዊ የክልሉን ስያሜ እና አርማ ተግባራዊ እንዲያደርጉ በጥብቅ ታዟል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: