#FastMereja I በትግራይ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በወጣ ይፋዊ ደብዳቤ፣ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የዞን እና የወረዳ አስተዳደሮች ከግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ህገ-መንግስታዊ ስያሜን፣ ብሄራዊ አርማን እና ማህተምን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ።
የክልሉ ምክር ቤት በሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ ወደ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ ለመመለስ መወሰኑ ይታወሳል። በዚህም መሰረት ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲሰራበት የነበረው የጊዜያዊ አስተዳደር መዋቅር የክልል መንግስት መተካቱ ተገልጿል።
ይህንን ተከትሎም ማንኛውም የመንግስት ተቋም በሚያደርጋቸው ኦፊሴላዊ ግንኙነቶች፣ የደብዳቤ ራስጌዎች (Letterheads) እና ማህተሞች ላይ “የጊዜያዊ አስተዳደር” የሚሉ ስያሜዎችን በመተው፣ የቀድሞውን ህገ-መንግስታዊ የክልሉን ስያሜ እና አርማ ተግባራዊ እንዲያደርጉ በጥብቅ ታዟል።
Source: FastMereja









No comments yet.