የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤር ትርዒት ለጎብኚዎች ክፍት ሆነየአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ 80ኛ ዓመት…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤር ትርዒት ለጎብኚዎች ክፍት ሆነ
የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው ልዩ የማይንቀሳቀስ የኤር ትርዒት (Static Air Show) ዛሬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በድምቀት ተከፍቷል።
አየር መንገዱ ባለፉት ሰማንያ ዓመታት በጽናት ተጉዞ ለደረሰበት ዓለም አቀፋዊ ስኬት ማስታወሻ ይሆን ዘንድ በተከፈተው በዚህ ዝግጅት ላይ፣ ታሪካዊና ዘመናዊ አውሮፕላኖች ለዕይታ ቀርበዋል።
ይህ ልዩ ትርዒት የአየር መንገዱን ጥንካሬና የደረሰበትን የላቀ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ አቅም ለጎብኚዎች በቅርበት የሚያሳይ ድንቅ አጋጣሚ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ በዓይነቱ ለየት ያለ ዝግጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአነስተኛ አጀማመር ተነስቶ እንዴት የዓለም ተመራጭ መሆን እንደቻለ ትውልድ ትምህርት እንዲቀስምበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ጎብኚዎች የአየር መንገዱን ታሪካዊ ጉዞ የሚያሳዩ ልዩ ኩነቶችን ከመመልከታቸውም በላይ፣ የደንበኞቹ የልብ አድራሽ የሆነውን የዚህን ታላቅ ተቋም የ80 ዓመታት የድል ጉዞ በጋራ እያከበሩ ይገኛሉ።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2