THE REMAKING OF ADDIS ABABA!!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ዛሬ የመፅናትና የማሸነፍ፣ የድላችንን አሻራ፣ የከተማችንን ለውጥ የታዘቡ የውጭ ሀገራት ፀሀፊዎችና ባህርማዶ የሚኖሩ ምሁራን በራሳቸው ተነሳሽነትና ገንዘብ ያሳተሙትን “THE REMAKING OF ADDIS ABABA/አዲስ አበባን እንደ አዲስ ” የተሰኘ መጽሐፍ ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት አስመርቀናል።

ይህ መጽሀፍ ለህዝባችን ቃል ገብተን፣ ቃላችንን በተግበር የቀየርንበትን ታሪክ የሚተርክ ነው። ሕዝባችን በገንዘቡ፣ በጉልበቱ፣ በሀሳቡ የተሳተፈበት የሁላችንም ውጤት ነው።

ከባህር ማዶ እንግሊዛዊው ጸሐፊዉ ኘሮፌሰር ስሞን ሊ፣ ዶ/ር ክሌመንት ካቱሉሺ፣ ትዉልደ ኢትዮዽያዊው ዶ/ ር ሂርዾ ቁምቢ እና ቡድናቸው በጋራ የጻፋት መጽሐፍ፣ ጠንካራ እሳቤ ወደ ተጨባጭ ስኬት መቀየሩን እና የአዲስ አበባን ትራንስፎርሜሽን ያሳየ እንዲሁም ለትውልድ የሚሻገር ታሪክን የሰነደ በመሆኑ ለጸሀፊዎቹ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

የባህር ማዶ ሰዎችን ቀልብ በሳበው የከተማችን ልማት፤ የሺዎች ድካምና ብርታት፣ የትወልድ አሻራ ለማሳረፍ የደከሙትን ሁሉ እውቅና እንሰጣለን፤ እናመሰግናለን!!!

የለውጥ ጉዞው የሁላችንም ኩራት ሲሆን፣ በቀጣይም ከተማችንን ይበልጥ ለማበልጸግ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: