“የአዶ ትዝታዎች” የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ መጪው ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ይመረቃል።

- Advertisement -
Sidebar AD

መጽሐፉ፤ የአንድ ቤተሰብን ታሪክ ዋቢ በማድረግ ከጉራጌ ማህበረሰብ ምድር ተነስተው ወደ አዲስ አበባ የተደረጉ ታሪካዊና ትውልድ ተሻጋሪ የህይወት ጉዞዎችን በስፋት የሚዳስስ ነው። በተለይም ውድ አያት ኑሮን ለማሸነፍ የከፈሉትን ከፍተኛ ተጋድሎ፣ ያጋጠሟቸውን አስገራሚ ክስተቶች በሳቅና በትዝታ ታጅቦ በሚያስነብብ መልኩ እንደተከተበ ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ የክቡር አባታችን የአቶ ወልደሚካኤል አንዳግቤ እና የውድ እናታችን የወ/ሮ አስካለ ኃብተማርያም ከጉራጌ ዞን እስከ አዲስ አበባ የዘለቀውን አስደናቂ የህይወት ጉዞ፤ ህይወትን ለመለወጥና ቤተሰብን ለመገንባት ያደረጉትን ተጋድሎ፣ ያፈሩትን ሀብትና ያጋጠሟቸውን ውጣ ውረዶች በግልጽ የሚያሳይ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ መጽሐፍ ፈጣሪ የሰጠንን ችሎታና ማስተዋል ለበጎ ነገር ማዋል እንደምንችል የምንማርበት፣ ከየትኛውም ከባድ ውድቀት መነሳት እንደሚቻል የሚያሳይና የትውልድ ቅብብሎሽን የሚያጸና የታሪክ መዝገብ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የመጽሐፉ የምረቃ ሥነ-ስርዓት ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከሜክስኮ ወደ መካኒሳ በሚወስደው መንገድ፣ ከሳር ቤት አደባባይ አለፍ ብሎ በስተቀኝ በኩል በሚገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቲዎሎጂካል ሴሚናሪ (EGST) አዳራሽ በድምቀት እንደሚካሄድ ታውቋል።

በዚህ ታላቅና ታሪካዊ የምረቃ በዓል ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ወዳጅ ዘመዶችና የመጽሐፍ አፍቃሪያን ተገኝተው የደስታው ተካፋይ እንዲሆኑ አዘጋጆቹ በአክብሮት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።




Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: