ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ የፈፀሙ ግብር ከፋዩች ቅጣትን ከ50 ሺህ ብር ወደ 100 ሺህ ብር ከፍ እንዲል የሚያደርግ የታክስ አስተዳ

- Advertisement -
Sidebar AD

ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ የፈፀሙ ግብር ከፋዩች ቅጣትን ከ50 ሺህ ብር ወደ 100 ሺህ ብር ከፍ እንዲል የሚያደርግ የታክስ አስተዳደር የማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጀ

በዛሬዉ እለት ለ10 አመት ሲሰራበት የቆየዉን የታክስ አስተዳደር አዋጅ ማሻሻያ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት እና ባለሙያዎች ጋር የግብአት መሰባሰብ ዉይይት አድርጓል።

በዚህ የማሻሻያ ረቂቅ ዉስጥ ተሻሽለው ከቀረቡ ነጥቦች መካከል ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ የሚፈፅሙ ግብር ከፋዩች ላይ ከዚህ ቀደም ቅጣት ተብሎ ተቀምጦ የነበረዉን የገንዘብ ቅጣት ከፍ ያደረገ ህግ ተቀምጦበታል።

በዚህም 50 ሺህ ብር ቅጣትን ያስቀምጥ የነበረዉን በማሻሻል የ100 ሺህ ብር ቅጣት የሚጥል አዲስ ህግ በረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ተቀምጧል።

ይህም በእያንዳንዱ ደረሰኝ የደረሰኙ ዋጋ ከግምት ዉስጥም የማይገባ ነዉ ተብሏል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የህግ አማካሪዉ አቶ ዋሲሁን አባተ እንደገለፁት “የተቀመጠዉ ገንዘቡ መጠን በግብር ከፋዩ ዘንድ እንደ አንድ ወጪ ታሳቢ እየተደረገ መጥቷል፤ ይህ ደግሞ ህገወጥነቱን እየጨመረ እንዲመጣ እያደረገ መጥቷል ብለዋል”።

ለዚህም ማሻሻያ እንዲደረግበት ሆኖ መቀመጡን ለዉይይቱ ተሳታፊዎች አስረድተዋል ።

በዚህ ሽያጭ ደረሰኝ ሳይሰጡ ሽያጭ በሚፈፅሙ ግብር ከፋይ በዚህ ድርጊት ከሁለት ጊዜ በላይ ከተገኙ ግን ወደ እስር የሚወስድ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚኖር አያይዘዉ ገልፀዋል።

Ethio Fm


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: