ዩክሬን ድሮኔ መንገድ ስቶ ኢስቶኒያ በመግባቱ ይቅታ ጠይቃለሁ አለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የዩክሬን የጦር ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በስህተት የኢስቶኒያን የአየር ክልል ጥሶ መግባቱን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ያስታወቀ ሲሆን፥ ድሮኑም በኔቶ የፀረ-አየር መከላከያ መትቶ መጣሉ ተገልጿል።

​ይህን ተከትሎ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄሮይሂ ትይኪ በኤክስ (X) ማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ኢስቶኒያን ይቅርታ እንጠይቃለን” በማለት ይፋዊ ይቅርታ ጠይቀዋል።

​ነገር ግን ለተፈጠረው የቴክኒክ ስህተት ሩሲያን ተጠያቂ ያደረጉት ሚኒስትሩ፥ “ሞስኮ ሆን ብላ የድሮኑን አቅጣጫ እንዲቀይር አድርጋለች” ሲሉ ክስ ሰንዝረዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
​#ዩክሬን #ኢስቶኒያ #ኔቶ #ሩሲያ #የአየር_ክልል_ጥሰት #Meduza #ThiqahEth


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: