#Ethiopia | የዩክሬን የጦር ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በስህተት የኢስቶኒያን የአየር ክልል ጥሶ መግባቱን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ያስታወቀ ሲሆን፥ ድሮኑም በኔቶ የፀረ-አየር መከላከያ መትቶ መጣሉ ተገልጿል።
ይህን ተከትሎ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄሮይሂ ትይኪ በኤክስ (X) ማህበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ኢስቶኒያን ይቅርታ እንጠይቃለን” በማለት ይፋዊ ይቅርታ ጠይቀዋል።
ነገር ግን ለተፈጠረው የቴክኒክ ስህተት ሩሲያን ተጠያቂ ያደረጉት ሚኒስትሩ፥ “ሞስኮ ሆን ብላ የድሮኑን አቅጣጫ እንዲቀይር አድርጋለች” ሲሉ ክስ ሰንዝረዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ዩክሬን #ኢስቶኒያ #ኔቶ #ሩሲያ #የአየር_ክልል_ጥሰት #Meduza #ThiqahEth
Source: GetuTemesgen






No comments yet.