የሁለት ወራት ደመወዝ የለም-ህወሓትበዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሃት ቡድን፣ በትግራይ ክልል ለሚገኝ ማንኛውም …

- Advertisement -
Sidebar AD
የሁለት ወራት ደመወዝ የለም-ህወሓት‼️
በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሃት ቡድን፣ በትግራይ ክልል ለሚገኝ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የግንቦት እና የሰኔ ወራት ደመወዝ እንዳይከፈል የሚል ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ።
ዶ/ር ደብረጽዮን ለክልሉ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ጭምር ባስተላለፉት የጽሁፍ ትዕዛዝ «ለሁለት ወራት ደሞዝ የለም፤ ይህንን ከወዲሁ እወቁት» ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ለውሳኔው እንደ ምክንያት የቀረበው የሀብት ውስንነት መኖሩ እና ፍትሃዊ የደመወዝ ማስተካከያ ለማድረግ መታሰቡ ቢሆንም፣ ቡድኑ «ፌደራሉ በጀት ከልክሎናል» በማለት አስቸኳይ የሀብት ማሰባሰብ ስራ እንዲጀምርም አዟል።
ይህ ይፋዊ መግለጫ «የበጀት እጥረት» ቢለውም፣ ታዛቢዎችና የፖለቲካ ተንታኞች ግን ውሳኔው ህወሃት ለሌላ አዲስ ጦርነትና ወታደራዊ ግጭት እያደረገው ያለውን ስውር ዝግጅት የሚያሳይ ግልጽ ማሳያ ነው ይላሉ።
ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ክልል ትምህርት ግንቦት 30 እንዲያበቃ ወስኗል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1