አርሰናል የፕሪሚየር ሊጉ አዲስ ንጉሥ!
#Ethiopia | ማክሰኞ ሜይ 19/2026 በእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ ትልቅ ምዕራፍ ተመዝግቧል።
ሙሉ ግምት ተሰጥቶት የነበረው ማንቸስተር ሲቲ በቦርንማውዝ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጠንካራ መከላከልና ማጥቃት ፈተና ገጥሞታል።
ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ሲቲዎች ከአርሰናል ጋር የነበራቸውን የነጥብ ልዩነት ማሻሻል ሳይችሉ ቀርተዋል።
ባለፉት ዓመታት የነበራቸውን የበላይነት ለማስቀጠል ከፍተኛ ጫና ውስጥ የነበሩት ሲቲዎች በዚህ ጨዋታ ያሳዩት መርበትበት እና ነጥብ መጣል ከዋንጫ ፉክክሩ ውጪ አድርጓቸዋል።
ይህ የሲቲ መሰናከል ግን ለሰሜን ለንደኑ መድፈኞች እውነተኛ ሰርግና መልስ ሆኖላቸዋል። የአርሰናል ደጋፊዎች የመጨረሻውን የእሁድ ጨዋታ ሳይጠብቁ ለአመታት የናፈቃቸውን እና በቅርብ ርቀት እያመለጠ ያስቸገራቸውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ባለቤት መሆናቸውን ቀድመው አረጋግጠዋል!
የኤምሬትስ ምሽት በደስታ ቀውጢ ሆኖ አምሽቷል።
🔴 የ22 ዓመታት የዋንጫ ናፍቆት አከተመ!
ሰሜን ለንደን በደስታ አብዳ አምሽታለች። ቀይና ነጭ የለበሱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች የተሰማቸውን ወደር የለሽ ደስታ ለመግለፅ በኤምሬትስ ስታዲየም ዙሪያ ተሰብስበው ነበር።
ለንደንን ባማረ ቀለም ባደመቁ ሪችቶች፣ በዘፈንና በጭፈራ ታሪካዊውን ምሽት አድምቀውታል። ስታዲየሙ ፊት ለፊት የነበረው የደጋፊው እቅፍ፣ ጭፈራ እና የእንባ ድብልቅ ደስታ ለዓመታት ለተደረገው ተጋድሎ የሚመጥን እውነተኛ የቀይ ምንጣፍ አቀባበል ነበረ።
ይህ ድል ለአንድ ትልቅ ክለብ ዳግም መወለድን ያበሰረ ታሪካዊ ክስተት ነው። አርሰናል ለአመታት በብዙ ውጣ ውረዶች፣ በተስፋ መቁረጥ እና በጠንካራ ተፎካካሪዎች መሀል አልፎ እዚህ የድል ጫፍ ላይ ደርሷል። ለክለቡ ቦርድ፣ ለተጫዋቾቹ፣ ለደጋፊዎቹ እና በተለይም ለአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከረጅም ጊዜ ትዕግስት በኋላ ፕሮጀክታቸው ፍሬ ማፍራቱን ያረጋገጡበት ታላቅ ምሽት ነበር።
አርሰናል ሻምፒዮንነቱን ቀድሞ ቢያረጋግጥም እስካሁን ድረስ ይፋዊ መግለጫ አላወጣም። ይሁን እንጂ እንደዚህ አይነት ታላቅ ድል ሲመዘገብ ክለቡ እና የለንደን ከተማ አስተዳደር የሚያደርጓቸው ዋና ዋና ዝግጅቶች የሚበሰሩት የመጨረሻው የሊጉ ጨዋታ ከተደረገ በኋላ መሆኑ የተለመደ ነው።
የክፍት አውቶቡስ ሰልፍ፦
ተጫዋቾቹ እና አሰልጣኞች ታሪካዊውን ዋንጫ ይዘው በክፍት አውቶቡስ ላይ በመሆን ደስታቸውን ይገልጻሉ።
የጉዞ መስመር፦
ጉዞው ከኤምሬትስ ስታዲየም ተነስቶ በኢስሊንግተን ጎዳናዎች ላይ ይደረጋል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ሰሜን ለንደን ጎዳና ላይ ወጥተው በጋራ እንደሚያከብሩት ጥርጥር የለውም።
የረጅም ጊዜ ትዕግስት እና የፕሮጀክቱ ፍሬ በመሆኑ ለመድፈኞቹ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚከፍት ነው።
ምንግዜም ድል ለመድፈኞቹ!
✍️
ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን) 🇬🇧
#Arsenal #EPLChampions #Arteta #EmiratesStadium #ManCity #NorthLondonIsRed #የአርሰናልዋንጫ #ስፖርትዜና
Source: GetuTemesgen









No comments yet.