የታይዋን የወደፊቱ ጊዜ የሚወሰነው በ’ውጫዊ ኃይሎች’ አይደለም ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናገሩ የታይዋን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ላ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የታይዋን የወደፊቱ ጊዜ የሚወሰነው በ’ውጫዊ ኃይሎች’ አይደለም ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ተናገሩ
 
የታይዋን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ላይ ቺንግቴ የታይዋን የወደፊት እጣ ፈንታ በ”በውጭ ሃይሎች” መወሰን የለበትም ይልቁንም በ23 ሚሊዮን ዜጎቿ እጅ ውስጥ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሁለተኛ አመት የስልጣን ዘመናቸዉን አስመልክቶ ላኢ እንደተናገሩት እንደ ፕሬዝዳንትነት የእኔ ግብ 180 ኪ.ሜ የውሃ መንገድ ታይዋንን ከቻይና የሚከፍለውን በታይዋን ባህር ዳርቻ ሰላም እና መረጋጋት ማስቀጠል እና “የውጭ ኃይሎች” የደሴቲቱን የፖለቲካ ሁኔታ እንዳይለውጡ መከላከል ነው ብለዋል ።
 
 
እ.ኤ.አ. በ 2016 ከታይፔ ጋር ያለውን ግንኙነት ካቋረጠችው ቤጂንግ ጋር ለመሳተፍ አሁንም ፈቃደኛ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል ፣ ነገር ግን በ “እኩልነት እና ክብር” መርሆዎች ላይ በተመሰረተ “ሥርዓት ልውውጥ” ብቻ ነው ሲሉ አክለዋል ።ታይዋን ኃላፊነት የሚሰማት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አባል እንጂ “መረጋጋትን የምትጎዳ አይደለችም” ብለዋል።
 
ላ በፕሬዚዳንትነት የ24 ወራት ዘመናቸዉ ውዥንብር ገጥሟቸዋል፣ ከዉስጥ እና ከውጭ ጨምሮ ከባህላዊ አጋር ዩናይትድ ስቴትስ ጋር ፈተና አሳልፈዋል፡፡በተቃዋሚ ቁጥጥር ስር ያለው ህግ አውጪ የፊርማ ልዩ የመከላከያ በጀት ከ40 ቢሊየን ዶላር ወደ 25 ቢሊየን ዶላር በማሳነስ በዚህ ሳምንት በታክስ ገቢ አለመግባባት ፕሬዝዳንቱን ከስልጣን ለማዉረድ እና ለመክሰስ ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካም፡፡
በስምዖን ደረጄ
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2