በድንገት ራሱን አ•ጥ•ፍ•ቶ!!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ሁሌም ስታገኙት ደስተኛና ሳቂታ የነበረ ሰው በድንገት ራ•ሱ•ን አ•ጥ•ፍ•ቶ ሞተ ሲባል ሰምታችሁ ታዉቃላቹ ?

ብዙ ሰዉ የድብርት ህመም ደስተኛ አለመሆን ፣ የሀዘን ስሜት ፣ ተስፋ መቁረጥ እና የመሳሰሉት ብቻ ይመስለዋል። አንዳዴ እየሳቁ እና እየተጫወቱ በከባድ የድብርት ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች አሉ።

ይህ በህክምናው Atypical Depression ተብሎ የሚታወቀው የድባቴ ህመም አይነት ሲሆን ከውጪ ለሚያያቸዉ ሰው ሳቂታና ደስተኛ ሊመስሉ ይችላሉ።

አብዛኛዉን ጊዜ ደስ የሚያሰኝ ነገር ሲያገኙ ለተወሰነ ጊዜ መደሰት ከዛም መልሶ የሀዘን እና የባዶነት ስሜት ዉስጥ መግባት፣ ምግብ ፍላጎት እና ክብደት መጨመር፣ ከሳምንታት በላይ ቀኑን ሙሉ መድከም እና እንቅልፍ ማብዛት፣ በትንንሽ አስተያየቶች እና ትችቶች መሰበር፣ የዘወትር ተግባራትን ለመከወን መቸገር የድባቴ ህመም ሌላኛዉ መልክ ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ የሳቀ ሁሉ ደስተኛ አይደለም ምናልባት ከሳቁ ጀርባ የተደበቀ የባዶነት እና የሀዘን ስሜት ይኖራልና እርስ በእርስ እንጠያየቅ።

የአዕምሮ ጤና ግንዛቤ ወር

ዶ/ር ኃይለልዑል መኮንን (የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት እና ካዉንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: