ሻዕቢያ በመቀሌ ቢሮ
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው የባይቶና ፓርቲ አመራር የሆኑት አቶ ክብሮም በፋና ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ፣ በክልሉ ወቅታዊ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ እጅግ ጠንከር ያሉና አነጋጋሪ ትችቶችን ሰንዝረዋል።
አመራሩ በትነተናቸው እንዳብራሩት፣ የኤርትራ መንግስት (ሻዕቢያ) በመቀለ ከተማ ውስጥ ምንም ዓይነት ታፔላ ወይም መለያ ምልክት የሌለበት ድብቅ ቢሮ በመክፈት፣ “ፅምዶ” ከተባለው ስብስብ ጋር በፈጠረው ውህደት አማካኝነት በትግራይ ምድር ላይ እንደልቡና ያለ ምንም ከልካይ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ይህ ዓይነቱ አሰራር በክልሉ ውስጥ ያለውን የህግ የበላይነትና የፀጥታ ቁጥጥር ጥያቄ ውስጥ የሚከት ከመሆኑም በላይ፣ በትግራይ ህዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ ከፍተኛ ስጋትና ምስቅልቅል የሚፈጥር መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል።
በተጨማሪም አቶ ክብሮም በዚሁ የፋና ቲቪ ቆይታቸው፣ በትግራይ ክልል ለረጅም ዓመታት በስልጣን ላይ የቆየውን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሃት) ፓርቲን ክፉኛ ተችተዋል።
ህወሃት ባለፉት ዓመታት የተከተላቸው የተሳሳቱ የፖለቲካ መስመሮችና የወሰዳቸው ውሳኔዎች የትግራይን ህዝብ ለከፍተኛ መከራ፣ ስደትና ውድመት የዳረጉ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ድርጅቱ በተግባር የትግራይ ህዝብ ዋነኛ አጥፊ ነው ሲሉ በደፍረት ተናግረዋል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.