📌በአየር ንብረት መዛባት ሳቢያ የመርዛማ እባቦች ፍልሰትና የንክሻ አደጋ በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት አመለከተ
#Ethiopia | የአለም ሙቀት መጨመር መርዛማ እባቦች ቀድሞ ከሚኖሩባቸው ስፍራዎች በመውጣት የሰው ልጅ በብዛት ወደሚንቀሳቀስባቸው የእርሻ ቦታዎችና የመኖሪያ መንደሮች እንዲሰደዱ እያደረጋቸው ሲሆን፣ ይህም ከሰዎች ጋር ያላቸውን ንክኪና የአደጋውን መጠን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል።
በጥናቱ መሰረት በተለይም በአፍሪካ የሚገኙት የሚተፉ ዘንዶዎች (Spitting Cobras) እና በእስያ የሚገኙት ክራይቶች (Kraits) የሙቀት ማዕበሉን ለማምለጥ ሰፊ የቦታ ለውጥ እያደረጉ መሆኑ ተረጋግጧል።
ዘ ጋርዲያን የዓለም ጤና ድርጅትን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፣ አገራት አደጋውን ለመከላከል በገጠራማ አካባቢዎች ለሚገኙ የጤና ተቋማት በቂ የእባብ መርዝ ማክሸፊያ መድኃኒቶችን (Anti-venom) እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#የአየርንብረትመዛባት #የእባብንክሻ #የአለምጤናድርጅት #የአለምሙቀት #የጤናመረጃ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.