አዲስአበባን ክልል እናደርጋለን ሲል ኢዜማ አስታወቀኢዜማ ቀጣዩን ሃገራዊ ምርጫ  የሚያሸንፍ ከሆነ አዲስአበባን ክልል ሊያደርግ …

- Advertisement -
Sidebar AD
አዲስአበባን ክልል እናደርጋለን ሲል ኢዜማ አስታወቀ
ኢዜማ ቀጣዩን ሃገራዊ ምርጫ  የሚያሸንፍ ከሆነ አዲስአበባን ክልል ሊያደርግ እንደሚችል በተወካዩ በኩል አስታወቀ ::
የኢዜማዉ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ከፋና ሚዲያ ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት ኢዜማ  ቀጣይ መንግስት ቢሆን የሃገሪቱን የክልል አወቃቀር በምን መልኩ ያዋቅራል የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል ፡፡
ለዚህም ምላሺ ሲሰጡ አዲስአበባን በማንሳት ከተማዋን ከአቅራቢያዋ ከሚገኙ ከተሞች ጋር በማጣመር ክልል እናደርጋለን ብለዋል ፡፡
አዲስአበባ ክልል የምትሆን ከሆነ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ማን ይሆናል ተብሎ ከጋዜጠኞች ጥያቄ የተነሳላቸዉ የኢዜማዉ ተወካይ በፓርቲዉ የክልል አወቃቀር ኦሮሚያ የሚባል ክልል እንዳማይኖር ጠቅሰዋል ፡፡
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2