#Ethiopia | ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ላለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ ሁነቶች ሲያከብር ቆይቶ በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነ ደማቅ ስነ ስርዓት ፍጻሜውን አድርጓል።
ባንኩ በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ የ30 ሚሊዮን ብር የበጎ አድራጎት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በልዩ የእድል ጨዋታው ላሸነፈ ደንበኛም የቢዋይዲ የኤሌክትሪክ መኪና በሽልማት አበርክቷል።
በዚሁ የምስጋና ምሽት ላይ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ እዮብ ተካልኝን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች፣ የጥበብ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ባንኩ ከጥር ወር ጀምሮ በኤግዚቢሽን፣ በፈጠራ ስራዎች ማበረታቻ እና በሴቶች አቅም ማጎልበቻ መርሃ ግብሮች ስኬታማ ቆይታ ማድረጉ ተገልጿል።
በታላቁ መዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ ዳሸን ባንክ አሁን ለደረሰበት ገናና ስም እና ስኬት የመሰረት ድንጋይ ለጣሉለትና ባንኩ እውን እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለክቡር ሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን ልዩ የማስታወሻ ሽልማትና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በተጨማሪም 11 የባንኩ መስራቾች፣ የቀድሞ የቦርድ አባላት፣ ስራ አስፈጻሚዎች እና ለረጅም ዘመን ያገለገሉ ሰራተኞች እንዲሁም ታማኝ ደንበኞች ተሸላሚ ሆነዋል።
የማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ባንኩ ባደረገው ውሳኔ መሰረት የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህጻናት ትምህርት እና ሙያ ስልጠና ለሚሰጠው ዲቦራ ፋውንዴሽን የ30 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አበርክቷል።
በሌላ በኩል በባንኩ ዘመናዊ መተግበሪያ አማካኝነት ሲካሄድ በቆየው የሽልማት እጣ የቢዋይዲ ሴጉል ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ለአሸናፊው ተጠቃሚ ተረክቧል።
#dashenbank #banking #anniversary #ethiopianfinance #deborahfoundation #corporatecharity #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen








No comments yet.