ላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ እና ፋስት ፔይ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia | በሀገር ውስጥ የሪል ስቴት እና የቤት ልማት ዘርፍ የተሰማራው ላይፍ ታይም ፕሮፐርቲ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ማስተላለፍ (ሐዋላ) አገልግሎት የሚሰጠው ፋስት ፔይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የስምምነት በዛሬው ዕለት በይፋ ተፈራርመዋል።

​በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰውአለ አባተ እንደገለጹት፤ ይህ ስምምነት በተለይ በውጭ ሀገር ለሚኖሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ክፍሎችና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ላይ ንብረት ማፍራት ሲፈልጉ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ሕጋዊና ተወዳዳሪ የሆነ የምንዛሬ ተመን ያለው የክፍያ ሥርዓት ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

​የፋስት ፔይ ተባባሪ መስራች እና ዋና የቴክኖሎጂ ኦፊሰር አቶ ሞቱማ ጊሹ በበኩላቸው፤ ከዚህ ቀደም በሪል ስቴት ዘርፍ ከክፍያ ጋር ተያይዞ የሚታዩትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እና ክፍያዎች በሕጋዊ መንገድ ብቻ እንዲፈጸሙና የደንበኞችን እምነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

በስምምነቱ መሠረት፣ ደንበኞች በፋስት ፔይ በኩል ክፍያ ሲፈጽሙ በየጊዜው ከሚለዋወጠው የገበያ ሁኔታ ጋር የሚሄድና ከባንክ የተሻለ እጅግ ተወዳዳሪ የሆነ የላቀ የምንዛሬ ተመን የሚያገኙ ይሆናል።

​ሁለቱ ተቋማት ያደረጉት ይህ ስምምነት በአሜሪካ እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ሕጋዊ እውቅና ያለውን የፋስት ፔይ የቴክኖሎጂ መሠረተ-ልማት በመጠቀም፣ የዳያስፖራውን ማኅበረሰብ የቤት ባለቤትነት ጉዞ በእጅጉ ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: