አሁን በስራ ላይ ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች ሰልጥነው የብቃት ምዘና አንዲወስዱ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት ሊዘረጋ ነው፡፡
ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ በማድረግ ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል I አጠቃላይ የሰነድ ዝግጅት ተጠናቋል ያለው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ነው፡፡
ይህ አዲስ አሰራር ከተለመደው አሰራር በተለየ መልኩ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፣ የምዘና ሂደቱ በዲጂታል ሲስተም እንዲመራ ተደርጎ ተቀርጿል ሲል ሚኒስቴር መ/ቤቱ መባህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መገለጫ ላይ ጠቅሷል ።
አሽከርካሪዎች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ቅድሚያ ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል ።
በዚሁ መሰረት ይህንን ሀገራዊ ፕሮጀክት በይፋ ወደ ትግበራ ለማስገባት በተለይም አጠቃላይ የአሽከርካሪዎች ምዝገባ እና ስልጠና በተመለከተ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከኤስ ዲ ኤስ ሴፍቲ ኤንድ ድራይቪንግ ስኪልስ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የስራ ውል ስምምነት መፈረማቸው ተሰምቷል።
በመሆኑም ይህ “ሀገር አቀፍ የአሽከርካሪዎች የብቃት ምዘና፣ የስልጠና እና የደህንነት ማሻሻያ ፕሮጀክት” የመንገድ የትራፊክ ደህንነትን በማጠናከር ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ተገምቷል፡፡
ማናቸውም አሽከርካሪዎች በሙሉ አዲሱን የብቃት ምዘና በመውሰድ እና በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ብቃታቸውን በተጨባጭ በማረጋገጥ ብቻ እንዲያሽከረክሩ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት ይዘረጋል ተብሏል።
ይህ አሰራር የመንገድ ደህንነትን በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ዜጎቻችን ብሎም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በመንገድ የትራፊክ አደጋ ምክንያት ሞትና የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት ውድመት ለመቀነስ ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑ ከፍተኛ እምነት ተጥሎበታል።
በመሆኑም ሁሉም አሽከርካሪ በዚህ ሂደት የሚያልፍ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይም ለዚህ ዙር በቅድሚያ ማንኛውም የንግድ ተሽከርካሪ የሚያሽከረክር አሽከርካሪ የምዝገባና የስልጠና እንዲሁም የምዘና ሂደቱ በቅርቡ ስለሚጀመር ሁሉም ዝግጁ እንዲሆን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሳስቧል።
Sheger Fm
Source: Yeneta Tube









No comments yet.