የማርሻል አርት ተወዳዳሪው ሴዶ ወደ ከቱርክ ቅድመ ኮበለለበቅርቡ ሙያዊ የውድድር ስምምነት (Professional Fight Con…

- Advertisement -
Sidebar AD
የማርሻል አርት ተወዳዳሪው ሴዶ ወደ ከቱርክ ቅድመ ኮበለለ
በቅርቡ ሙያዊ የውድድር ስምምነት (Professional Fight Contract) መፈረሙ የሚነገርለት የማርሻል አርት ተወዳዳሪ ሴዶ ማርሻል (Sedo Martial)፣ በአሁኑ ወቅት ከሀገር ውጪ መሆኑን ገልጾ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለመወዳደር ከፍተኛ የገንዘብና የንብረት ጥያቄዎችን የያዘ ቅድመ-ሁኔታ አቅርቧል።
ተወዳዳሪው በቱርክ አውሮፕላን ማረፊያ ሆኖ ባሰራጨው የቪዲዮ መልዕክት፣ ያለምንም በቂ ክፍያ «በነጻ» እንዲወዳደር ለቀረበለት ጥሪ ምላሽ እንደማይሰጥና በአደራዳሪዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለው በይፋ ተናግሯል።
ሴዶ ማርሻል ወደ ሀገሩ ተመልሶ ወደ መጋጠሚያው መድረክ (Ring) ለመግባት በአጠቃላይ የ70 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸውን ሦስት መስፈርቶች አስቀምጧል፡-
* የ20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ዋጋ ያለው ተሽከርካሪ፤
* የ30 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የመኖሪያ ቤት፤
* በቀጥታ ወደ ግል አካውንቱ ገቢ የሚደረግ 20 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር።
እነዚህ መስፈርቶች ተሟልተው አካውንቴ ላይ ከተገቡ ብቻ መጥቼ እደባደብላችኋለሁ፤ ካልሆነ ግን በነጻ የሚሆን ምንም ነገር የለም።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1