ሰኞ ግንቦት 24 ሥራ ዝግ ነው።ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም በፌዴራል እና ክልል መንግሥታዊ ተቋማት እንዲሁም የግል ተቋማት …

- Advertisement -
Sidebar AD
ሰኞ ግንቦት 24 ሥራ ዝግ ነው።
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም በፌዴራል እና ክልል መንግሥታዊ ተቋማት እንዲሁም የግል ተቋማት ሥራ ዝግ ሆኖ ይውላል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ቦርዱ፦
– ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
– ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑ እና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
– የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ እንዲያከነውኑ ፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት እንደማያስገድድ አሳውቋል።
– የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችን እና ዕቅዶችን እንዳይይዙ እና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ አበረታቷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1