“ የአርቴታ ንግግር ግልጽ ትዕቢት ነው ” ሮይ ኪን

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል አባላት የግል የውስጥ የደስታ ዝግጅት አዘጋጅተው ነበር።

በዝግጅቱ ላይ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ለድግሱ ታዳሚያን ያደረጉት ንግግር ሾልኮ ወጥቷል።

አሰልጣኙ ባሰሙት ንግግር “ ቅዳሜ ደግሞ በእርግጠኝነት የአውሮፓ ሻምፒዮን እንሆናለን “ ሲሉ ይደመጣሉ።

የአርቴታ ንግግር ቪዲዮ በኋላም እንዲጠፋ ቢደረግም በርካቶች ተቀባብለውት በማህበራዊ ሚዲያው በስፋት ተሰራጭቷል።

በክለቡ ውስጥ አርቴታ ስህተት ሰርተዋል የሚል እምነት ባይኖርም ንግግሩ የፒኤስጂ ተጨዋቾች ጋር ደርሶ ተጨማሪ ተነሳሽነት ይፈጥርላቸዋል የሚል እምነት እንዳለ ተገልጿል።

በዚህም የአርቴታ ንግግር የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ታሪካዊ ተጨዋች ሮይ ኪን ሾልኮ የወጣውን የሚኬል አርቴታ ንግግር ” ትዕቢት ” ሲል ገልጿል።

“ ግልጽ ትዕቢት ነው ” ሲል የገለፀው ሮይ ኪን ” እኔ በፒኤስጂ ቦታ ብሆን እና ይሄን ንግግር ብሰማ ወዲያው ነበር የመልበሻ ቤቱ ግድግዳ ላይ የምፅፈው ” ሲል ተናግሯል።

አክሎም “ አርቴታ ለእነሱ ነፀ የማነቃቂያ ንግግር አበርክቶላቸዋል “ ሲል ገልጿል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#tikvahethsport


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: