#FastMereja I የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ ባስተዋወቀው አዲስ እና የተሻሻለው የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ምክንያት በተወሰኑ ደንበኞቹ ላይ የአገልግሎት መስተጓጎል ማጋጠሙን አምኖ፣ ችግሩን በአፋጣኝ ለመፍታት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። ባንኩ ለተፈጠረው መስተጓጎል ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አገልግሎቱን ለማዘመንና የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር በርካታ አዳዲስ አማራጮችን ያካተተ የተሻሻለ መተግበሪያ በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ሆኖም መተግበሪያው አዲስ በመሆኑ ምክንያት በተወሰኑ ተጠቃሚዎች ላይ የአገልግሎት መቋረጥና መስተጓጎል አጋጥሟል። ባንኩ በአሁኑ ወቅት የቴክኒክ ችግሩን ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን፣ ችግሩ ተፈቶ አገልግሎቱ ወደ መደበኛ ሁኔታው ሲመለስ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።
Source: FastMereja









No comments yet.