የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ

- Advertisement -
Sidebar AD

ኢትዮጵያ ከቡሩንዲ

#Ethiopia | በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከቡሩንዲ አቻው ጋር ወሳኝ የመልስ ጨዋታ ያካሂዳል።

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚዘጋጀው የዓለም ኮከቦች መድረክ ለማለፍ በሚደረገው በዚህ ውድድር ላይ ብሔራዊ ቡድኑ በመጀመሪያው የቤት ጨዋታው በአዲስ አበባ አበበ በቂላ ስታዲየም 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።

የዛሬውን ወሳኝ የመልስ ጨዋታ ደግሞ በቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ በሚገኘው ኢንትዋሪ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ያደርጋል።

ለዚህ ጨዋታ የኢትዮጵያ ታዳጊ ቡድን ሙሉ ቢጫ መለያ ለብሶ ወደ ሜዳ እንደሚገባ የታወቀ ሲሆን ወደ ሦስተኛው ዙር የማጣሪያ ደረጃ ለመሸጋገር የዛሬውን ጨዋታ በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ብቻ ይበቃዋል።

#digitalhagerie #ethiopiau17nationalteam #worldcupqualification #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1