ፈተናውን ወደ መልካም አጋጣሚ የቀየረው የልዩ ህክምና ክሊኒክ፤ በዘመናዊ ህንጻና ግብዓቶች ስራ እንደገና ጀመረ

- Advertisement -
Sidebar AD

በከተማዋ በተካሄደው የኮሪደር ልማት ምክንያት አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረው ህንጻ የፈረሰበት የልዩ ህክምና ክሊኒክ፣ አቅሙንና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎቹን በከፍተኛ ደረጃ በማዘመን በአዲስ መልክ ተመርቆ ስራ ጀመረ።
ክሊኒኩ በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱን በስፋት መቀጠል የጀመረው በየካ ክፍለ ከተማ፣ ታቦት ማደሪያ እግር ኳስ ሜዳ አጠገብ ባስገነባው ባለ 22 ክፍል ዘመናዊ ህንጻ ላይ መሆኑ ታውቋል።
የተቋሙ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ዳዊት አማረ በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ እንደገለጹት፤ ክሊኒኩ የገጠመውን ፈተና ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር በይዘቱም ሆነ በህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እራሱን በከፍተኛ ደረጃ ማዘመን ችሏል።

ተቋሙ በተለይም በውስጥ ደዌ እና በሳንባ ስፔሻሊስት (Pulmonology) የህክምና ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ ጥራት ያለው አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ ለድንገተኛና ለአስቸኳይ ህክምና ፈላጊዎችም ቀልጣፋ አደረጃጀት ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
“ጤና የእያንዳንዱ ሰው መሰረታዊ መብት ነው” ያሉት ዶክተር ዳዊት፤ ባለፉት ስድስት ዓመታት በርካታ ታካሚዎችን በታማኝነት ሲያገለግሉ መቆየታቸውንና አሁንም ማህበረሰቡን በተሻለ ጥራትና ምቾት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን አብራርተዋል።
አዲሱ ህንፃ የህክምና ተቋም ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶችን ሙሉ በሙሉ ያሟላ ከመሆኑም በላይ፣ ህፃናትን ጨምሮ ማንኛውንም ታካሚ በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ የሚያስችሉ ባለሙያዎችና ዘመናዊ ግብዓቶች ተጠናቀውለታል። ተቋሙ በኮሪደር ልማት ምክንያት ቢፈርስም፣ ላለፉት 14 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥበት በነበረው በዚሁ አካባቢ ለታካሚዎች ምቹ በሆነ ስፍራ ላይ በላቀ አደረጃጀት ዳግም ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

ይህ የልዩ ህክምና ክሊኒክ ለ56 የህክምና ባለሙያዎች የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 23 የሚሆኑ ስፔሻሊስት እና ሰብ-ስፔሻሊስት ዶክተሮችን በማሳተፍ ላይ ይገኛል። በጥናት ማጠቃለያውም ላይ ክሊኒኩ ባለፉት ዓመታት አብረዋቸው ለቆሙ ታካሚዎች እና በአስቸጋሪ ወቅቶች ስራው ሳይስተጓጎል ድጋፍ ላደረጉ ባልደረቦቹ ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል።






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: