ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ ያንጊዜም ይጾማሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

የጾመ ሐዋርያት የጊዜ ቀመር ሥሌት በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት ተናግሮ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ በማቴዎስ 9÷14 እንደተጻፈው በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፣ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት፡፡ ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ “የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ ነገር ግን ” በመለት መለሰላቸው፡፡ እኔ ሳለሁ አይጾሙም ማለቱ እርሱ ካልሞተና ካላረገ፤ መንፈስ ቅዱስንም ካልላከላቸው በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት ጾመው ድል መንሳት ስለማይቻላቸው ነው፡፡

ስለዚህም ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ስለሁለት ዓላማ ይህን ጾም የአገልግሎታቸው መጀመሪያ አድርገውታል፡፡ አንደኛው ስለተሰጣቸው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ አምላካቸውን ለማመስገን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በዓለሙ ሁሉ ዞረው ለሚሰብኩት ወንጌል ራሳቸውን ለማዘጋጀት ነው፡፡ ይህን ጾም የምንጾመው ሐዋርያት ጾመው ጸልየው ድል ያደረጉትን ዓለም እኛም የምናሸንፍበት ኃይል እንዲሰጠን፣ ለቅዱሳን ሐዋርያት የተለመነ አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲለመነን ለመማጸን ነው፡፡ ይህ ጾም በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እድሜው ከሰባት ዓመት በላይ የሆነ ኦርቶዲክሳዊ ሁሉ እንዲጾመው በአዋጅ ከታዘዙ አጽዋማት አንዱ ነው፡፡ የሐዋርያትን ጾም አንዳንዶች “የቀሳውስት ጾም” ሲሉት ይሰማል፡፡

አንዳንድ ላለመጾም የሚፈልጉ ወገኖች “የሐዋርያት” የሚለውን ቃል ብቻ በመውሰድ ጥንት ይህንን ጾም ሐዋርያት እንጂ ሕዝቡ አልጾመውም፤ ስለዚህ ዛሬ ደግሞ በሐዋርያት እግር የተተኩ ካህናት ስለሆኑ ጾሙም የእነርሱ ብቻ ሊሆን ይገባል ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ በፍትሐ ነገስት አንቀጽ 15፡ 586 ግን ይህን ጾም አንዱ ካንዱ ሳይለይ ዕድሜው ከሰባት ዓመት በላይ የሆነ ሁሉ እንዲጾም ቤተ ክርስቲያን አውጃለች፡፡ እኛም እነርሱን ተከትለን፣ በእነርሱ ሥርዓት በመመራት፣ በሐዋርያት ላይ ያደረው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብት በእኛም ላይ እንዲያድርብን በየዓመቱ ጾመ ሐዋርያትን እንጾማለን፡፡ ዘመናቸውን በጸሎትና በጾም የሚያሳልፉት ገዳማውያንም ይህን ጾም በመጾም ታላቅ በረከት ያገኛሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1