“የትግራይን የተወረረ ሉዓላዊ መሬት እናስመልሳለን” አርሚ 33

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ​የትግራይ መከላከያ ኃይል ተብሎ የሚጠራው TDF አካል የሆነው አርሚ 33 ፣ ለሶስት ሳምንታት ሲያሰለጥን የቆየውን አቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው ዕለት አጠናቀቀ። ስልጠናው በተለይም በውትድርና ሳይንስ፣ በቴክኒክ ብቃት እና ወቅታዊ የፖለቲካ ትንተናዎች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደነበር ተገልጿል።

​በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአርሚ 33 አመራሮች፣ ስልጠናው የትግራይን የተወረረ ሉዓላዊ መሬት ለማስመለስ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እና በወረራ ስር የሚገኙ ወገኖችን ነጻ ለማውጣት የሚደረገውን ጥረት አቅም የሚገነባ መሆኑ ተገልጿል።





Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2