#Ethiopia | ዛሬ ይፋ በተደረጉት ውጤቶች ብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል እና በጋምቤላ ክልል፥ ለህዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤት ያቀረባቸው ሁሉም እጩዎች ወንበሩን አግኝተዋል።
በአማራ ክልል በጎንደር ዙሪያ 4 ምርጫ ክልል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እጩ የሆኑት አቶ ጣሂር ሙሐመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፓርቲያቸውን ወክለው ወንበር ሲያገኙ፤ በቀሪዎቹ ለህዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤት ብልጽግና ፓርቲ ያቀረባቸው እጩዎች ወንበሩን አግኝተዋል።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ወክለው ለክልል ምክር ቤት የተወዳደሩት ሀሲል አርባብ ሀሚስ አንድ መቀመጫ ሲያገኙ፥ ብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ክልሉ ለክልል ምክር ቤት ያቀረባቸው 8 እጩዎች መቀመጫ አግኝተዋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ዛሬ ውጤታቸው ይፋ የተደረጉ የምርጫ ክልሎች አንድ ፓርቲ ብቻ የተወዳደረባቸው እና በድምጽ ቆጠራው አሸናፊ በሆኑትና ከታች ባሉት መካከል ያለው የድምጽ ልዩነት “በሺዎች” ልዩነት ያላቸው መሆኑን አስረድተዋል።
በሌላ በኩል ሰብሳቢዋ ምርጫ ከተካሄደባቸው 1,138 የምርጫ ክልሎች ውስጥ 816 የሚሆኑት የማዳመር ሥራቸውን አጠናቀው ወደ ማዕከል ውጤታቸውን መላካቸውን አስታውቀዋል ያለው ቲክቫህ ነው።
ቦርዱ ይፋ የተደረጉ ውጤቶችን በዌብሳይቱ ላይ እንደሚለጥፍ ገልጿል።
#ማስታወሻ ፦ ከላይ የቀረቡት ውጤቶች ቦርዱ በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረጋቸውን ብቻ የሚመለከት ነው።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.