እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

መልአኩ ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መገባት🙏

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ገና በቅድስት ሐና ማሕጸን ከነበረችበት ወቅት ጀምሮ ተአምራት ታደርግ ነበር፡፡ አንድ አይኗን ያጣች ቤርሳቤህ የተባለች ሴት የሀናን መጽነስ ስትሰማ በደስታ ልትጎበኛት መጣች፡፡ ቅድስት ሐናን እንኳን ደስ አለሽ ብላ ሆዷን ከዳሰሰቻት በኋላ በዚያው እጇ ዓይኗን ብትነካው ዐይኗ በርቶላታል፡፡ ይህን ምሳሌ አደርገው ድውያን እየመጡ ሆዷን ዳሰው ይፈወሱ ነበር፡፡ በመካንነት የነበሩት ወላጆቿ ልጅ ከሰጣቸው ለቤተ እግዚአብሔር ሊሰጡ ስዕለት ገብተው በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ ፍሬ ሲያገኙ ዓለም ደግሞ የመድኃኒቱን እናት አጊኝቷል፡፡ እናታችን ቅድስት ሐና ጸንሳ ሳለች የአጓቷ ልጅ አርፎ እጅግ የአልጋውን ሸንኮር እየዞረች ስታለቅስ ከሞተበት ተነስቶ “የሰማይና የምድር ፈጣሪ አያት ሆይ ላንቺ ክብር ይገባሻል” ብሎ መስክሮ ተመልሶ አርፏል፡፡

አይሁድም “ቀድሞ የእነዚህ ዘር የነበሩ ዳዊትና ሰሎሞን አርባ፣ አርባ ዘመን ገዙን አሁን ከዚህች የሚወለድ ምን ሊያደርገን ነው?” ብለው በድንጋይ ሊወግሯት ተነሱ፡፡ የራማው ልዑል ቅዱሰ ገብርኤል ወደ ሊባኖስ ተራራ ወሰዳቸው፤ በእዚያም በጨለማ ውስጥ የነበረው ዓለም ብርሃን የሚያይባት፣ የእውነተኛው ጸሐይ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸው አስታውሰው በሦስት ዓመቷ ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሲሰጧትም ካህኑ ዘካርያስ ስለምግቧ ተጨንቆ፤ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ሊቀበል ሲቀርብ ወደ ላይ ራቀበት፡፡ በዚያ በተሰበሰቡትም ቢሞክሩ አልሆነም፡፡

ዘካርያስም ሐናን “እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ” አላት፤ በዚያም ጊዜ ቅድስት ማርያም እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መግቧት፤ በክብር ዐረገ፡፡ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም “የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር” ብለው ታህሣስ 3 ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡ ለ12 ዓመታትም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ይህችን ብርሃን፣ የብርሃን እናት ገዳማውያን አባቶችና እናቶች ዘወትር በጸሎታቸው ያስቧታል፡፡ ገዳማቸውን እናግዝ፣ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: