የሰከንድ ስሌት እና የ”ሩት ቢር” ናፍቆት ጥበብ በክንድ ላይ ስትመለክ!

- Advertisement -
Sidebar AD

⌚️

በአሁኑ ዘመን የሰዓት አገልግሎት ጊዜን ማወቅ ብቻ አይደለም ጊዜውን የሚቆጥረው አካል ማንነት፣ የውበት ምርጫ እና ምናልባትም “የኪስ አቅም” ማሳያ ጭምር እንጂ።

ሰሞኑን በዲጂታሉ ዓለም የብዙዎችን አይን የሳበውና መነጋገሪያ የሆነው የስዊዘርላንዶች እጅግ ረቂቅ የእጅ ጥበብ ውጤት የሆነው Rolex GMT-Master II “Root Beer”ሰዓት ነው።

ይህ ሰዓት እንዲሁ ተራ የሰከንድ መቁጠሪያ አይደለም በስፖርታዊ ጥንካሬው እና በቅንጦት ውበቱ የብዙዎችን ልብ የሰረቀ የሰዓት አምራቾች ቁንጮ ነው።

የ”ሩት ቢር” ቀለም እና የቅንጦት ጥበብ

ይህ ሞዴል “Root Beer” የሚለውን ስም ያገኘው ከባህላዊው መጠጥ ቀለም ጋር በሚመሳሰለው ከሴራሚክ (Cerachrom) ከተሰራው ቡናማ እና ጥቁር ጠርዙ የተነሳ ነው።

ሰዓቱ የትዕግስት፣ የጥራት እና የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ውጤት ነው።

* *ሁለት ዓለም በአንድ ክንድ ላይ**

ይህ ሰዓት የተሰራው በተለይ በተደጋጋሚ ለሚጓዙ ሰዎች በመሆኑ በአንድ ጊዜ የሶስት የተለያዩ ሀገራትን የሰዓት ቀጠናዎች መቁጠር ይችላል።

የEverose ወርቅ እና የብረት ቅይጥ

ሮሌክስ የራሱን የፈጠራ መብት የተጠቀመበትን የሮዝ ወርቅ (Everose Gold) እና ልዩ ብረትን አቀናጅቶ የሰራው በመሆኑ፣ በሩቅ ሲመለከቱት እንኳ ማራኪነቱ አይን ይበላል።

ይህንን ሰዓት ልዩ የሚያደርገው ውበቱ ብቻ አይደለም ወደ ገበያው ሲመጣ የሚጠይቀው አስገራሚ የገንዘብ መጠን ጭምር ነው።

በሮሌክስ መደብሮች ውስጥ ሰዓቱን ለማግኘት እጅግ ረጅም የጥበቃ ዝርዝር (Waiting List) ያለ ሲሆን በዓለም አቀፍ የግራጫ ገበያ (Grey Market) ላይ ደግሞ ዋጋው እስከ አስር ሺዎች አሜሪካ ዶላር ድረስ ይተመናል።

የዚህን ሰዓት ዋጋ ወደ እኛ ሀገር የመግዛት አቅም እና የወርሃዊ ደሞዝ ስሌት ስንመዝነው ነገሩ ሌላ ታሪክ ይወልዳል።

በአንድ በኩል ጥበብን የሚያደንቅ አይን እንዲህ ያለውን ውድ ዕቃ በክንድ ላይ ማየቱ “የእውነትም ያምራል!” ሊያስብል ይችላል።

በሌላ በኩል ግን የኑሮው ፈተና እና የኪስ አቅሙ ሁኔታ ፈታኝ በሆነበት ምድር ላይ እንዲህ ያሉ የቅንጦት ቁንጮዎች በአደባባይ ሲታዩ “የቁጥሮቹ ስሌት እንዴት ይሆን?” የሚል የብዙዎችን የማወቅ ጉጉትና የትዝብት ጥያቄ መቀስቀሱ አልቀረም።

ታዲያ ጊዜው የቴክኖሎጂ ነውና ሰዓቱ ራሱ በአንድ ጊዜ የሶስት የተለያየ ሀገር ሰዓቶችን እንደሚቆጥረው ሁሉ ሰዓቱን የሚያዩ ሰዎችም በአንድ ጊዜ ሶስት የተለያየ ሀሳቦችን ቢያሰላስሉ አይገርምም አንደኛው የሰዓቱን ውበት ያደንቃል፣ ሁለተኛው ዋጋውን ሰምቶ ይደመማል፣ ሶስተኛው ደግሞ “ይህንን የመሰለ ወርቅ በደሞዝ ወይንስ በምን?” ብሎ በዝምታ ይተክዛል።

ያም ሆነ ይህ ሰዓቱ ግን አሁንም ስራውን በትክክል እየሰራ ነው ሰከንዶችን ያለ ማቋረጥ ይቆጥራል ጊዜ ደግሞ ሁሉንም ነገር ..


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: