ኬንያ በኢንተርፖል ጥያቄ የሱዳኑን ፖለቲከኛ ያሲር አርማንን በቁጥጥር ስር አዋለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሱዳን ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ያሲር አርማን፣ የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ መሪ ሲሆን የኢንተርፖል የእስር ማዘዣ ለናይሮቢ ከደረሰ በኋላ የኬንያ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው መቻሉ ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

እ.ኤ.አ. በመስከረም 2024 መገባደጃ ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አል ፈትህ ታይፉር ሚያዝያ 15 ቀን 2023 በጀመረው ጦርነት ከፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች ጋር በመተባበር ፖለቲከኛውን በመክሰስ የእስር ማዘዣ የተጣለባቸውን የሲቪል ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ማስተባበሪያ ወይም ታጋዱም መሪዎችን ማሳደድ መጀመሩ ይታወቃል። የተሳዳጆቹ መሪዎች ዝርዝር የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን እና በርካታ የሃምዶክ አገዛዝ መሪዎችን ያካተተ ነው።

የኬንያ ፖሊስ ያሲር አርማን ናይሮቢ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ በማስቆም የእስር ማዘዣ እንደወጣበት ተነግሮት በቁጥጥር ስር ውሏል። ከዚያም ክሱ የወንጀል ወይም ፖለቲካዊ ስለመሆኑ ምርመራ እስኪደረግ በከተማው በሚገኝ ሆቴል ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል ተብሏል።

አርማን በናይሮቢ አውሮፕላን ማረፍያ ከኢንተርፖል የተገናኙ ሰዎች ካነጋገረ በኋላ ወደ ናይሮቢ ሆቴል ተዛውሯል። በሱዳን ህግ እና አለም አቀፍ የሰብአዊ ህግ ጥሰት የተከሰሰው አርማን ለሱዳን መንግስት ተላልፎ እንዲሰጥ ከሱዳን አቃቤ ህግ በይፋ ጥያቄ ቀርቧል። አርማን በሱዳን ስላለው ሁኔታ ከምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ጋር ለመገናኘት ወደ ኬንያ ያቀና ሲሆን ይህ ሳይሆን ቀርቶ በቁጥጥር ስር ዉሏል።

ነገር ግን ምንጮቹ የኬንያ ባለስልጣናት አርማን በአስቸኳይ እንዲፈቱ እና የፖርት ሱዳን መንግስት የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹን ለመክሰስ የአለም አቀፍ ህግጋትን ለመጠቀም የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም አሳስበዋል።
#BisratFm

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1