#Ethiopia | ኢመርጂንግ ሚዩዚክ ላብ የተሰኘው በማቲዎስ ወንዱ-የኢትዮጵያ የካንሰር ሶሳይቲ የስነልቦና እና ማህበራዊ ድጋፍ ማዕከል ልዩ የሙዚቃ ምሽት አካሂዷል።
በዶ/ር አስገዶም ኃይሌ እና በፕ/ር ስቬን ሽናይደር የተመሰረተው ኢመርጂንግ ሚዩዚክ ላብ የኢትዮጵያን ቅላፄዎች ከምዕራባውያን አዘፋፈን ስልቶች ጋር በማዋሃድ አዲስ እና የሚማርክ ድቅል ድምፅ መፍጠር የቻለ ልዩ ጥምረት ነው።
በአዳዲስ የሙዚቃ አቀራረቦችና ውብ ዜማዎች የታዳሚውን ልብ መማረክ የቻለው ጥምረቱ በማዕከሉ ያረፉ የካንሰር ታካሚዎች፣ ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ታዳሚው የማይረሳ ምሽት እንዲያሳልፍ ማድረግ ችሏል።
ማቲዎስ ወንዱ-የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ አቶ ወንዱና ቤተሰቦቻቸው ልጃቸው ማቲን በካንሰር ምክንያት ማጣታቸው የፈጠረባቸውን መሪር ሃዘን ወደ ስኬት ለመቀየር በማሰብ ያቋቋሙት የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ሶሳይቲው ላለፉት 20 ዓመታት የህፃናትና የአዋቂዎች ካንሰርን ጨምሮ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን ለመዋጋት በሚደረገው ሀገር አቀፍ ጥረት ውስጥ ዘርፈ ብዙ ሚና ተጫውቷል።
ሶሳይቲው እስከዛሬ ከ3000 በላይ ታካሚዎችንና ቤተሰቦቻቸውን የደገፈ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በፓንጋሲሊ የስነልቦና እና የማህበራዊ ድጋፍ ማዕከል ከ140 በላይ ለሚሆኑ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ማዕከሉ ለታካሚዎች የምግብ፣ የማረፍያ፣ የትራንፖስርት፣ የመድሃኒትና የምርመራ ወጪ ከመሸፈን አልፎ ተኝተው ለሚታከሙና በህክምና ላይ ሆነው ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ታካሚዎች በየወሩ አበል ይሰጣል።
በአንድ ቤተሰብ የተጀመረ ታሪካዊ ተልዕኮ ይህን ያህል ለውጥ ካመጣ በጋራ ብንተባበር ምንያህል ታካሚዎችን ማገዝ እንደምንችል አስበውታል? ማዕከሉን በመጎብኘት ከልጆቹ ጋር ጊዜ ማሳለፍ እንዲሁም ከእኛ ጋር በመስራት የካንሰር ታካሚዎቻችንን መደገፍ ለምትፈልጉ በሚከተሉት ስልኮች ታገኙናላችሁ። 0915583544 / 0919893919/ 0936821229
የምታደርጉት እያንዳንዱ አስተዋፅኦ የካንሰር ታማሚ ህጻናት ምግብ፣ መጠለያ፣ መድሃኒትና የምርመራ አገልግሎት እንዲያገኙ ብሎም ከህመማቸው እንዲያገግሙ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል።



Source: GetuTemesgen









No comments yet.