ስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) ምንድነው?

- Advertisement -
Sidebar AD

ስፓይና ቢፊዳ በእርግዝና ወቅት በአፈጣጠር አለመስተካከል ምክንያት የሚከሰት የአንጎልና ህብለ ሰረሰር መጎዳት ነው፡፡

በዓለም ላይ ከሚወለዱ አንድ ሺ ህፃናት መካከል ከሁለት እስከ ሶስት የሚሆኑት ከዚህ ጉዳት ጋር አብረው ይወለዳሉ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሃገሮች ቁጥሩ ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡

መንስዔው ምንድነው ?

ስፓይና ቢፊዳ በአብዛኛው የሚከሰተው እናቶች ከእርግዝና በፊትና በመጀመሪያዎቹ ሶስት የእርግዝና
ወራት ሰውነታቸው ውስጥ ፎሊክ አሲድ የሚባል የቫይታሚን እጥረት ሲከሰት ነው፡፡

በስፓይና ቢፊዳ የተጠቁ ህጻናት እንደተወለዱ የሚታይ ያልተለመደ እብጠት በአብዛኛው ጊዜ ጀርባቸው ፤ የራስ ቅላቸው እና ከኃላ አንገታቸው ላይ ይከሰታል፡፡

ከስፓይና ቢፊዳ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ችግሮች ምንድናቸው ?

ከስፓይና ቢፊዳ ጋር የተወለዱ ህፃናት ለተለያዩ ችግሮች የሚጋለጡ ሲሆን የችግሩ መጠንም እብጠቱ እንደወጣበት ቦታና ጥልቀት ይወሰናል፡፡

ከስፓይና ቢፊዳ ጋር በተያያዘ ከሚከሰቱ ችግሮች መሃል በጥቂቱ ፡-

🔹የህፃኑ ጭንቅላት በውሃ መሰል ፈሳሽ መሞላትና ትልቅ መሆን (ሃይድሮሴፋለስ)
🔹የአንጎልና ህብለሰረሰር ኢንፌክሽን (ሜኒንጃይተስ)
🔹ከወገባቸው በታች አካል መስነፍና በእግራቸው ቆመው ለመሄድ አለመቻል
🔹ሽንትና ሰገራን መቆጣጠር አለመቻል
🔹የአከርካሪ አጥንቶችና የእግር መጣመም
🔹ሌሎች ለመንቀሳቀስ ካለመቻል ጋር ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ ችግሮች

ህክምናዎቹ ምን ምን ናቸው?

በስፓይና ቢፊዳ ህመም የተጎዱ ህፃናት ህክምና ያስፈልጋቸዋል፡፡

እንደተወለዱ በጀርባቸው ወይም በጭንቅላታቸው ላይ የሚታየው እብጠትና ክፍተት አስቸኳይ የቀዶ ህክምና ሊደረግለት ይገባል፡፡

ከዚያም የህፃኑ የጭንቅላት ፈሳሽ ሲያጠራቅም ማለትም ሃይድሮሴፋለስ ሲከሰት ለችግር የሚያስፈልግ የቱቦ ማስገባት ቀዶ ህክምና ያስፈልጋል፡፡

በተጨማሪም የማይቋረጥ የህክምና ክትትል እና ሌሎች ተጨማሪ ቀዶ ህክምና ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

ችግሩ እንዳይከሰት እንዴት መከላከል ይቻላል ?

🔹ማንኛዋም በእርግዝና እድሜ ክልል ውስጥ ያለች እናት በየቀኑ በፎሊክ አሲድ ቫይታሚን የበለፀጉ ምግቦችን እንድትመገብ እና የፎሊክ አሲድ ቫይታሚን እንድትወስድ ይመከራል፡፡

🔹በዕቅድ ለማርገዝና ልጅ ለመውለድ ያሰበች እናት ሐኪም በማማከር ከማርገዟ በፊት ለሁለት ወራት እና ከአረገዘች በኃላ ደግሞ ለሶስት ወራት ተጨማሪ የፎሊክ አሲድ ቫይታሚን እንክብል እንድትወስድ ይመከራል፡፡

በፎሊክ አሲድ የበለጸጉ ምግቦች የትኞቹ ናቸው?

አብዛኞቹ በአካባቢያችን የሚገኙ ምግቦች በውስጣቸው ፎሊክ አሲድ ይዘው ይገኛሉ፡፡

ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹ ፡-

🔸ምስር
🔸ጎመን
🔸አቮካዶ
🔸የዶሮ ስጋ

▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🏆 “ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ፤ የሀገርዓቀፍ ጥራት ሽልማት የ3’ኛ ደረጃ የልህቀት ዋንጫ ተሸላሚ!” 🏆

▬▬▬▬▬▬▬▬▬

“መኖራችን ለእርስዎ ነው!”

“OUR EXISTENCE IS FOR YOU!”


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: