በሰው አንጎል ሴሎች የሚሰራ ኮምፒዩተር ይፋ ሆነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በሰው አንጎል ሴሎች የሚሰራ የዓለማችን የመጀመሪያው ኮምፒዩተር በአውስትራሊያ ይፋ ሆኗል፡፡

በላቦራቶሪ በበለጸጉ የሰው አንጎል ኒውሮን ሴሎች የሚሰራው ይህ ኮምፒዩተር ‘ሲኤል አንድ’ የተሰኘ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በባርሴሎና በተካሄደው የ’ሞባይል ወርልድ ኮንግረስ’ ላይ ለእይታ የቀረበው ኮምፒዩተሩ በሰው ሰርሽ አስተውሎት እና በሮቦቲክስ ዘርፎች አዲስ ምዕራፍ መክፈቱ ተነግሯል፡፡

የስነ-ህይወት የአስተውሎት ስርዓትን የሚከተለው ‘ሲኤል አንድ’ ኮምፒዩተር ፤ በውስጡ እስከ 6 ወራት በህይወት መቆየት የሚችሉ ኒውሮን ሴሎችን ይዟል፡፡

ቅንጣት በምታክል ሲልከን ቺፕ ውስጥ የሚቀመጡት ሴሎቹ ፤ የህይወት ድጋፍ የሚሰጥ የሙቀት እና የጋዝ መቆጣጠሪያ ስርዓት እንደተገጠመላቸው ታውቋል፡፡

ኮምፒዩተሩ እስካሁን ከተሰሩት የሰው ሰርሽ አስተውሎት የቴክኖሎጂ ውጤቶች በእጅጉ የላቀ ፈጣን የመማር እና የመላመድ አቅም እንዳለውም ያሆ ኒውስ ዘግቧል፡፡

የኮምፒዩተሩ የፈጠራ ባለቤት የሆነው ‘ኮርቲካ ላብስ’ የተባለው ተቋም ፤ ይህን ቴክኖሎጂ በተለያዩ ዘርፎች ለማካተት እየሰራ እንደሚገኝም አመላክቷል፡፡
#etv

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2